ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Monday 22 October 2018

ዕለተ ሰኞ አመሻሽ ላይ የወጡ አጫጭር የዝውውር ዜናዎች፣ የእግር ኳስ ወሬዎች እና አስተያየቶች



➦  የሪያል ማድሪድ ቦርድ ጆዜ ሞሪንዎን የክለቡ አዲስ አለቃ በማድረግ ጁሊያን ሎፕቲግን እንዲተካላቸው ቀዳሚ ምርጫ አድርገውታል። ሎስብላንኮዎቹ አሰልጣኙን ለማባረስ ወስነዋል። (el chiringuito).

.

➦  ጆዜ ሞሪንዎ ማን.ዩናይትድ ከቼልሲ ጋር ከመጫወቱ ቀደም ብሎ የቡድኑን ቋሚ አሰላለፍ ማን እንዳወጣው ተጭዋቾቹ ላይ ማጣራት ያደርጋሉ። ሞሪንዎ የቡድኑ ቋሚ አሰላለፍን በማህበራዊ ገፆች ቀድሞ በማየቱ ተበሳጭቷል።  (mail)

.

➦  የአርሰናል ደጋፊዎች አሮን ራምሴይ ለክለቡ ከፈረመ 10ኛ አመቱ መምጣቱን ተከትሎ የክለቡ ቦርድ የዌልሳዊውን አማካይ ፍላጎት በማሟላት በኤምሬትስ ለተጨማሪ አመታት የሚያቆየውን ኮንትራት እንዲያስፈርሙት ግፊት ለማሳደር ልዩ የማህበራዊ ሚዲያ ቅስቀሳ ዘመቻ ጀምረዋል።  (Thesun)

.

➦  ሞሪንዎ በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ የክለቡ ቦርድ አንድ መሃል ተከላካይ እንዲያስፈርምላቸው ለመጠየቅ አስበዋል። አሰልጣኙ በሰይዶ ኩሊባሊ ደረጃ ያለ ተከላካይ የሚፈልጉ ሲሆን ተጭዋቹም ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የመዛወር ፍላጎት አለው።
(Duncan Castles)

.

➦  ፓትሪስ ኤቭራ በስታምፎርድ ብሪጁ የቼልሲ እና ማን.ዩናይትድ ጨዋታ ላይ ከክለቡ ሊቀመንበር ኢድ ውድዋርድ ጋር ሆኖ ታይቷል። ከውድዋር ጋር በተደጋጋሚ መታየቱን ተቀጠለው ኤቭራ ለዚዳን ከወዲሁ መስራት ጀምራል የሚሉ ጥርጣሬዎችን አበራክቷል።  (MEN)

.

➦  ክሮክስ: "ሁሉም ሰው ሃድስፊልድ ላይ የማሸነፊያዋን ጎል ሲያስቆጥር ሞሃመድ ሳላህ ያገባትን ኳስ ስላቀበለው ሻቂሪ ነው ሚያወራው የኔ ግን ይለያል። ለኔ ግን ኳሷ የጎሜዝ ነበረች የርሱ ውጤት ናት"  (Anfieldhq)

.

➦  ጀርገን ክሎፕ እንደሚያምኑት ከሆነ ቡድናቸው በዚህ የውድድር አመት ያሳየው መጠነኛ የአጨዋወት ዘዬ ለውጥ እንዴት ያረጀች ውሻን ንክሻ ማስተማር እንደሚቻል ያሳየንበት አቀራረብ ነው ብለዋል። 

"ሁልግዜም ቢሆን አጥቅተህ ስለተጫወትክ ታሸንፋለህ ማለት አይደለም። ምክንያቱም በርህን ሁሌም ትከፍታለህ ስለዚህ ሜዳውን ስላሰፋሃው በተቃራኒ ቡድን ትነከሳለህ" ሲሉ አንዳንዴም መከላከል እንዳለባቸው ተናግረዋል።
(liverpoolecho)

.

➦  ማንቸስተር ሲቲዎች አዲስ የተከላካይ አማካይ ለማዛወር የክረምቱን የዝውውር መስኮት ለመጠበቅ ይገደዳሉ። የሲቲዎች ስም በተደጋጋሚ ግዜ ከአያክሱ አማካይ ዲ ጆንግ እና ከዎልቭሱ ሩበን ኔቬስ ጋር እየተያያዘ ይገኛል።   (ESPN FC)

.

➦  ቦሩሲያ ዶርትመንዶች በቡድናቸው ድንቅ አቋም እያሳየ ካለው እንግሊዛዊው ጃደን ሳንቾ ዝውውር በኃላ አይናቸውን በሊጉ ክለቦች ታዳጊዎች ላይ የጣሉ ሲሆን ሦስት ተጭዋቾች ላይ አማትረዋል። እነርሱም ፊል ፎደን (Manchester City), ቦቢ ዱንካን (Liverpool የቀድሞ የCity) እና ካሉም ሁድሰን ኦዶዪ (Chelsea) ናቸው።  [Mirror] 

.

➦  ማንቸስተር ሲቲዎች በባለፉት አራት አመታት ላይ ብቻ ከአካዳሚያቸው ታዳጊ ተጭዋቾችን በመሸጥ የ £70m ሂሳብ ገቢ አግኝተዋል። ከነርሱ መሃከል ጃዶን ሳንቾ፣ ማርኮስ ሎፔስ፣ ፓብሎ ማፎዎ እና ጃሰን ዲናየር ይገኙበታል። (Mirror)

.

➦  ኤዲን ሃዛርድ ክለቡ ቼልሲ ወሳኝ ጨዋታዎችን የሚያደርግበት ሳምንት ላይ ቢሆንም ጉዳት ደርሶበት እንዳይሆን አስግቶአቸዋል። ማውሪዚዮ ሳሪ ሃዛርድ እንደተፈራው የሚጎዳባቸው ከሆነ ተፎካካሪዎቻችን መከተል ይከብደናል ብለው ይሰጋሉ።
(MirrorSport) 

.

➦  ቼልሲዎች ለኤዲን ሃዛርድ ሳምንታዊ የ £350,000 ደሞዝ በማቅረብ ቤልጂየማዊውን ኮከብ የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛው ተከፋይ ሊያደርጉት ቆርጠዋል።   (Source: Sunday Express) 

.

➦  ሪያል ማድሪዶች የጥር የዝውውር መስኮት ሲከፈት ዝላታን ኢቭራሞቪችን ለማዛወር ያልተጠበቀ ጥያቄ ሊያቀርቡለት አስበዋል። የጎል ድርቅ ቀውሱን በመጠኑም ቢሆን እንደሚቀርፍላቸው አስበዋል።
(Source: Daily Mirror)

.

➦  ኡናይ ኤምሬ: “በኤምሬትስ ያደረግነውን ያለፈውን ጨዋታ የምናስታውሰው ከሆነ (ከዋትፎርድ ጋር የተጫወቱትን) ጨዋታውን አሸንፈናል። ሆኖም በምንፈልገው መልኩ መጫወት ግን አልቻልንም። ጨዋታውን በአግባቡ መቆጣጠር አልቻልንም ነበር። ለኔ አሁን አስፈላጊው ነገር የምንፈልገውን አጨዋወት እስክናገኝ ድረስ አለመቸኮል ነው ጊዜ ያስፈልገናል።"

.

➦  "የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪዱን የኤል ክላሲኮ ጨዋታ አልከታተልም። ምክንያቱም የማይረባ 'It's s***' ጨዋታ ነው"  - ሲል የቀድሞው የሌስተር ሲቲ ተከላካይ ሮበርት ሁዝ ለምን የEl Clasico ጨዋታ እንደሚጠላው አስገራሚ አስተያየቱን ሰጥቷል።
(dailymail)

No comments:

Post a Comment