ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Monday 5 November 2018

ሰኞ ምሽት የተሰሙ ሠፋ ያሉ ልዩ-ልዩ ዜናዎች News You Missed Today



THEY THINK CIT'S ALL OVER ማንቸስተር ሲቲዎች ትላንት ያስመዘገቡት የ6ለ1 ድል እንግሊዝ ያሉ ደጋፊዎች ሊቨርፑል እና ቼልሲ በሊጉ ዋንጫ ፉክክር ላይ እጅ መስጠት አለባቸው ሲሉ መወያያ አድርገውታል

የፔፕ ጋርዲዮላ ልጆች ሳውዛምፕተኖችን በመረምረም በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ አናት ላይ ተመልሰው የወጡ ሲሆን ማህበራዊ ትስስር ገፆችን በደጋፊዎች በሊጉ ዋንጫ ተስፋ መቁረጥ አስተያየቶች አጨናንቀውት ውለዋል

MANCHESTER CITYዎች የተቀናቃኞቻቸው ቡድን ደጋፊዎች ከወዲሁ ተስፋ እንዲቆርጡ የሚያደርግ ፐርፎርማንስ ሳውዛምፕተኖች ላይ በማስመዝገብ ደጋፊውን አነጋግረዋል። የተለያዩ ክለቦች ደጋፊዎች በትዊተር እና በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች በሰጡት አስተያየት መሰረት ሲቲዎች ከወዲሁ ሊጉን አስሸንፈዋል። ይህን እንዲሉ የገፋፋቸው ነጥብ የጋርዲዮላው ቡድን ማሸነፉ ብቻ ሳይሆን ያስቆጠራቸው ግማሽ ደርዘን ጎሎች እና ያስቆጠሩበት መንገድ ናቸው።

ራሂም ስተርሊንግ ያስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ተደምረው የጋርዲዮላው ቡድን ሊጉ ከተጀመረበት ያለፈው አመት አንስቶ በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ አምስት እና ከዚያ በላይ ጎሎችን በማስቆጠር ያሸነፏቸውን ጨዋታዎች ብዛት ወደ አስር አሳድገዋል።

________________________________________

➦  የሰማያዊዎቹ ቼልሲዎች አለቃ ማውሪዚዮ ሳሪ እንዳሉት ከሆነ ሁለት የቡድናቸው ተጭዋቾች እርሳቸው ከሚፈልጉት ስብስብ ትርፍ በመሆናቸው ክለቡን መልቀቅ ይችላሉ።

ዳኒ ድሪንክወተር እና ቪክተር ሞሰስ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ከስታምፎርድ ብሪጅ መውጫ በር ላይ ያሉ ተጭዋቾች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

MAURIZIO SARRI እንዳብራሩር ከሆነ ዳኒ ድሪንክ ወተር እና ቪክቶር ሞሰስ ክለቡን።ም ለመልቀቅ ነፃ ናቸው። ሁለቱም ለአሰልጣኙ ፎርሜሽን የሚመቹ አይደሉም።

ድሪንክወተር በዚህ የውድድር አመት ላይ ገና አንድም የነጥብ ጨዋታ ላይ ያልተሳተፈ ሲሆን ሞሰስ በበኩሉ በአንቶኒዮ ኮንቴ ዘመን የቡድኑ ቁልፍ ሰው የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በሊጉ ሁለት ጊዜ ብቻ ተቀይሮ በመግባት መጫወት ነው የቻለው።

________________________________________

➦  በእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ጎል እንደማስቆጠር በደስታ የሚያስፈነጥዝ ክስተት አለ ቢባል ማጋነን አይሆንም። ሆኖም ለቬንዙዌላዊው አጥቂ ግን ክስተቱ ይበልጥ በደስታ ላይ ደስታ የደረበለት ጎል ሆናለች።

በቺሊ ፕሪሚየራ ዲቪዥን ጨዋታ ላይ አጥቂው ኤድዋርድ ቤሎ ለክለቡ አንቶፋጋስታ ጎል ካስቆጠረ በኃላ ደስታውን የገለፀበት መንገድ ግን አነጋጋሪ ሆኑአል።

ቡድኑ ምንም እንኳን በጫዋታው ላይ 3ለ2 ቢሸነፍም ጎል ላስቆጠረው አጥቂ ኤድዋርድ ቤሎ ግን መቼም  የሚረሳ ጨዋታ አይሆንም። ተጭዋቹ ጎሉን ካስቆጠረ በኃላ ቀጥታ ወደ ተጠባባቂ ተጭዋቾች ቦታ አምርቶ አነስ ያለ የታሸገ እቃ ነገር በመያዝ በቅርብ ተቀምጣ ወዳለችው ፍቅረኛው ጋር ሮጦ በማምራት ከፊቷ ተንበርክኮ የጣት ቀለበት አወጣና "ታገቢኛለሽ ውዴ!" ሲል ጠየቃት። በሁኔታው የተደናገጠችው ፍቅረኛው በልዩ ደስታ ስሜት ተውጣ "አዎ አገባሃለው ውዴ" ስትል ፈቅዳ እዛው ቀለበቱን አድርጎላታል።

________________________________________

➦  የርገን ክሎፕ ከሬድ ስታር ቤልግሬድ ጋር ላለባቸው የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ስኳዳቸውን ይፋ አደረጉ..

በዚህ መሰረት ነገ ጨዋታው ላይ የሚሳተፉ ተጭዋቾች ዝርዝር ይሄንን ይመላል ፦

CONFIRMED SQUAD FOR BELGRADE: Fabinho, Van Dijk, Wijnaldum, Lovren, Milner, Keita, Firmino, Mane, Salah, Gomez, Alisson, Sturridge, Moreno,
Lallana, Mignolet, Robertson, Origi, Solanke, Matip, Kelleher, እና Alexander-Arnold ናቸው።

________________________________________

➦  IN OR OUT? ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎናው ቀጣይ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ቡድን ውጪ በመሆኑ ደጋፊዎቹን አስደነገጠ - ከቆይታ በኃላ ደግሞ መልሶ የቡድኑ አካል ተደረገ

ባርሴሎናዎች በኢንተር ሚላኖች የቻምፒየንስ ሊግ ዝግጅት ላይ የሳይኮሎጂ ጨዋታ ለመጫወት ሞክረዋል። ይሄንን ያደረጉት የሊዮኔል ሜሲ ጤንነት ጉዳይን በጥርጣሬ ውስጥ በመግለፅ ነው።
አርጀንቲናዊው ኮከብ በማክሰኞው ጨዋታ ቡድን ውስጥ መጀመሪያ ተካቶ ነበር ከዛም መልሰው ከስኬዱ ውጪ አደረጉት ከዛም በድጋሚ ወደ ሚላን የሚያመራው የተጭዋቾች ቡድን ስብስብ ውስጥ አስገቡት - ይሄንን ያደረጉት በሰአታት ልዩነት ውስጥ ነው።


________________________________________

➦  THE ANALYST በሚለው አርዕስት በSunSport ጋዜጣ አምደኝነት የሚፅፈው ዳኒ ዳኒ ሂጊንቦታም የአርሰናሎች ደካማ ተከላካይ ክፍል ክፍተት የተደፈነውን በሚስጥራዊው መሳሪያቸው ሉካስ ቶሬራ ነው ሲል አድናቆቱን በመቸር ፅፎለታል

አርሰናሎች ከሊቨፑል ጋር በተጫወቱበት ወቅት ያሳዩት ድንቅ የቡድን እንቅስቃሴ ነጥብ ይዘው እንዲወጡ ያደረጋቸው ሲሆን በዚህ ሲዝን የሊጉ ውድድር ላይ እውነተኛ የሻምፒየንስ ሊግ ቶፕ-4 ተፎካካሪ መሆናቸውን ያሳዩበት ጨዋታ ነው ሲል ፅፏል።

TORREIRA IS KEY

ለዚህ ሁሉ የአርሰናል ጥብቅ የኃላ መስመር ሽፋን በመስጠት ተከላካዮቹን ሲሸፍን የነበረው ሉካስ ቶሬራ ነው። ለቡድኑ ነጥብ መጋራት የሱ አስተዋፅዎ ትልቅ ነበር።

እርሱ ባልተሰለፈባቸው አምስት ጨዋታዎች ላይ መድፈኞቹ 10 ጎሎችን ሲያስቆጥሩ 9 ጎሎች ግን ተቆጥሮባቸዋል።

እርሱ በተጫወተባቸው 6 ጨዋታዎች ግን 15 ጎሎችን አስቆጥረው 5 ብቻ ገብቶባቸዋል።

አራቱን የተከላካይ ክፍል በሚገባ ይሸፍናል። አጥቂዎቹ በነፃነት ወደፊት እንዲሄዱ ያደርጋል። ተመላላሽ ተከላካዮቹ ያለስጋት ወደፊት እንዲሄዱ ያደርጋል ሲል ለቡድኑ ስኬት ተጭዋቹን አድንቌል።


________________________________________

➦ ጆዜ ሞሪንዎ ለክለባቸው ችግር ፊታቸው ወደ ክለቡ የቀድሞ ተጭዋቾች ጋሪ ኔቭል እና ሪያን ጊግስ ሆቴል ላይ አዙዋረል።

ቡድናቸው ባለፉት ሁለት የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ ወደ ስቴዲየሙ መድረስ ካለባቸው ሰአት አርፍደው በመምጣታቸው በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ለቅጣት እና ለማስጠንቀቂያ ተዳርገው ነበር።

ይሄንን ችግራቸውን ለመቅረፍ ታዲያ ማንቸስተር ዩናይትዶች ቡድናቸው በሜዳው ጨዋታዎችን ከማድረጉ በፊት ተጭዋቾቹ እስከ ጨዋታው መዳረሻ ድረስ ከኦልትራፎርድ በቅርብ ርቀት ላይ በሆነው የጋሪ ኔቭል እና የሪያን ጊግስ Hotel Football ውስጥ እንዲያርፉና በዛው ወደ ስቴዲየሙ እንዲሄዱ ለማድረግ ያቀዱ ሲሆን ከሆቴሉ ባለቤቶች እና ከቀድሞ ተጭዋቾቻቸው ጋር ለመነጋገር አስበዋል። (Source: Sun Sport)



No comments:

Post a Comment