ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Friday 9 November 2018

የሳዎ ፖሎውን የ24 አመት ኮከብ ዳንኤል ኮሪያን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ አመነ

መርማሪዎች እንዳረጋገጡት ከሆነ ግድያ የተፈፀመበት እግር ኳስ ተጫዋች ዳንኤል ኮሪያ በወቅቱ 'በጣም ጠጥቶ' ስለነበር 'ሴት ለመድፈር የሚያበቃ አቅም አልነበረውም' ሲሉ መርማሪዎች ተናግረዋል

የሳዎ ፖሎው ኮከብ ኮሪያ በብራዚሏ Sao Jose dos Pinhais ከተማ ባሰቃቂ ሁኔታ ኦክቶበር 27 ተገሎ የተገኘ ሲሆን አንገቱ እና ብልቱ ተቆርጠው ነበር በድን እሬሳውን ፓሊስ ያገኘው።

የቢዝነስ ሰው ናቸው የሚባሉት የ38 አመቱ ኢድሰን ጁኒየር ከሦስት ቀናት በኃላ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን የ24 አመቱን ኮከብ እግር ኳስ ተጭዋች እብደት ባለው በዛች ሌሊት ባለቤቴን ክርስቲና ብሪቴስ ለመድፈር ሙከራ ሲያደርግ በመድረሴ ገድዬዋለሁ ሲል አምኖአል።

ኮሪያ ከክርስቲና ጋር አልጋ ላይ እያለ የተነሳውን ፎቶ ለሳዎ ፖሎው የቡድን አጋሩ ልኮለት ነበር። ከዛም ወደ አንድ ፓርቲ ድግስ ቤት ናይት ክለብ ለመዝናናት በድጋሚ አምርቶ ነበር።

ክርስቲና እና ኢድሰንን የሚወክሉት የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ "በተጭዋቹ ያለፍቃዷ በተኛችበት ወሲብ እንድትፈፅም ሞክሮአል። ወሲብ ሊያደርጋትም ታግሏል"

"ዳንኤላም በወቅቱ ጠጥታ ነበር። እንቅልፍ ላይም ነበረች። ሁኔታው ህልምም መስሏት ነበር። ስትነቃ እርሱ መሆኑን ተመለከተች ከዛም በጩሃት የድረሱልኝ ጥሪዋን አሰማች"

ሆኖም መርማሪ አማኤዱ ትሪቪዛን ይሄንን መላምት ተችተዋል እናም ያሉት መረጃዎች የተሰጠው መግለጫ ጋር አይጣጣሙም ብለዋል።

እንደተባለው ከሆነ በምርመራው ወቅት እንደተገኘው የtoxicology ውጤት ሪፖርት ከሆነ ኮሪያም ጠጥቶ ነበር እናም ክሪስቲናን ለመድፈር የሚያበቃ ተፈጥሮአዊ አቅሙን አጥቷል።

በMail ሪፖርት እንደተደረገው, ትሪቪዛን ሲያክሉ: "
"ከሰማናቸው የአይን እማኞች እና በወቅቱ በቤቱ ውስጥ ከነበሩ ሰዎች እንደተረዳነው ከሆነ ክሪስቲና እንደተባለው ጥቃት እየደረሰባት በመሆኑ ስትጮህ ማንም ሰው አልሰማም ጩሃትም አላሰማችም።

"ማንም ሰው ደግሞ የኤድሰንን በሩን በጉልበት ሰብሮ ሲገባ ድምፅም አልተሰማም። ትልቅ ቤት አልነበረም ክፍሉ አነስተኛ ቤት ነበር። ብዙ ሰዎችም በዙሪያው እዛው ነበሩ"

"እኛ እንደምናምነው ከሆነ ኤዲሰን ኤዲሰን ወንጀሉን ከመፈፀሙ በፊት ባካባቢ የነበሩ ሰዎች ዝም እንዲሉ አግባብቷቸዋል።

"ስለዚህ የክርስቲና ሰዎች እየዋሹ እንደሆነ እናስባለን። ሆን ብለውም የራሳቸውን ታሪክ እየፈጠሩ ነው። ውንጀላው ሃሰት መሆኑን ለማረጋገጥ የፈጠሩት የታሪክ ፍሰት ነው።" ብለዋል።

ኤዲሰን እንዳለው ከሆነ ክፍሉን ሰብሮ ለመግባት የተገደደው ከውስጥ ተቆልፎ ስለነበር ነው። ከውስጥ ደግሞ የክርስቲና የድረሱልኝ ድምፅ ከውጪ ሆኖ ሰምቶታል።

"ከዛም ከሚስቴ ሰውነት ላይ አነሳሁት እና ወደ ወለሉ ወረወርኩት። ያንን ወንከለኛ በቻልኩት ሁሉ ሚስቴን ከመድፈር አዳንኩአት። ያደረኩት ያንን ነው።"

"በጣም ደጋግሜ መትቼዋለሁ። ቀጥቅጬዋለሁ። ከዛም ከቤት ውጪ ይዤው ሄድኩ በህይወት ይኑር ወይ እራሱን ስቶ ይሆን የማውቀው ነገር አልነበረም። ግን አይኖቹን ከድኖ ነበር።

"በወቅቱ ምንም የማስበው ነገር አልነበረም። በመኪናዬ ውስጥ ቢላዋ ነበር። አነስ ያለ ስለታማ ቢላዋ። ከዛም ምን ማድረግ እንዳለብኝ አይምሮዬ ሹክ አለኝ። የሆነውን ሁሉ አደረኩ"

No comments:

Post a Comment