ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Saturday 10 November 2018

ውለታ መላሹ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ (በመንሱር አብዱልቀኒ)



  የትልቁ ስፖርቲንግ ሊዝበን መልማዮች እንደሚመጡ ሲሰማ ለምልመላ የተዘጋጁት ታዳጊዎች ጓጉተው ጠበቁ። የልጅነት ህልማቸው እውን እንዲሆን አጋጣሚው ከእንቁ በላይ ውድ ነበር። ክሪስቲያኖ ሮናልዶ የተባለው ታዳጊም በቡድኑ ውስጥ እንዳለው እኩያው አልበርት ፋንትሮ ሁሉ ምኞቱ ከዚህ የተለየ አልነበረም።

መልማዮቹ እንደመጡ ታዳጊው ሁሉ ራሱን ለገበያ ሊያቀርብ ያቺን ቀን ያለ የሌለ ብቃቱን ሁሉ አውጥቶ ሊያሳይ ቆረጠ።

መልማዮቹ ማን የስፖርቲንግ ሊዝበንን አካዳሚ ነጻ የስልጠና ዕድል እንደሚያገኝ ለታዳጊዎቹ ማስገንዘቢያ ተናገሩ።

"የበለጠ ጎሎችን ያስቆጠረ ይመለመላል" ተባለ።

በጨዋታው ክሪስቲያኖ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጠረ። አልበርት በአስደናቂ ቴስታ ሁለተኛውን ጎል በስሙ አስመዘገበ።

ውጤት 2ለ0 ሆኖ ጨዋታው ቀጠለ።

ሶስተኛዋ ጎል ግን ተመልካቹን ሁሉ ያነጋገረች ሆነች። ከሁለቱ ተጫዋቾች አንድ ጎል የጨመረ በጨዋታው የሚፈለገውን የጎል የበላይነት ይይዛል። ፉክክሩ ልብ አንጠልጣይ በሆነበት ሰዓት አልበርት ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ-ለ-አንድ ተገናኘ። ራሱ ጎሉን ማስቆጠርና ስኮላርሺፑን ለራሱ ማድረግ  ይችላል። ከበረኛው ፊት ሲደርስ ግን ዕድሉን አሳልፎ ሰጠ።

ራሱን ነፃ አድርጎ ወደ ጎል ለተጠጋው ክሪስቲያኖ አመቻችቶ አቀበለው። ሮናልዶም ከመረቡ ውስጥ ዶላት።

ጨዋታው 3ለ0 ሲያበቃ፣ ክሪስቲያኖ ለስፖርቲንግ አካዳሚ ስኮላርሺፕ ታጨ።

ከጨዋታው በኋላ ሮናልዶ ወደ አልበርት ሄዶ ጠየቀው።

"ከቶ እንዴት ዕድሉን አሳልፈህ ሰጠኸኝ?"

የአልበርት ምላሽ አጭርና ግልፅ ነበር።

"ምክንያቱም አንተ ከእኔ የበለጠ ተሰጥኦ ስላለህ፣ ዕድሉ ላንተ ስለሚገባ ነው" አለው።

ፈፅሞ የማይታመን ነበር። ከዓመታት በኋላ ሮናልዶ ይህን ታሪክ ሲናገር የሰማ ጋዜጠኛ የተባለው እውነት ለመሆኑ ማስረጃ ፍለጋ ወደ አልበርት ፋንትሮ ቤት ሄደ።

የጎለመሰው አልበርት ፕሮፌሽናል ተጫዋች አልሆነም። ይባስ ብሎ ከዚያ ጨዋታ በኋላ የእግር ኳስ ተጫዋችነት ህይወቱ እንዳበቃ ለጋዜጠኛው ነገረው። አሁን የረባ ስራ እንኳን እንደሌለውም አስረግጦ አጫወተው።

ጋዜጠኛው ግራ ገባው።

"እንዴ?… የረባ ስራ እንኳን የለህም። ግን ይህን በሚያክል የተንጣለለ ቪላ ውስጥ ትኖራለህ። የበርካታ መኪኖች ባለቤት ነህ። በተጨማሪ ቤተሰብህን አንደላቀህ ታኖራለህ። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሃብቱ ከየት መጣ?"

አልበርት ለመልሱ አልተቸገረም።

"ይህን ሁሉ ያደረገልኝ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ነው።"

በተወዳጁ ጋዜጠኛ መንሱር አብዱልቀኒ የተፃፉ ሌሎች ተመሳሳይ መሳጭ የእግርኳስ ታሪኮችን ከታች አስቀምጠንላችኃላ ፦

የትንሹ ሊዮኔል ሜሲ ህልም እና ቢፔ
ያቺን ምሽት ፖል ስኮልስ፤ ያ ማልያ አንድሬስ ኢኔሽታ (የአሸናፊውና ተሸናፊው ወግ)
ጆዜ ሞሪንዎ ያቺን ሰዓት

ምንጭ ፦ መንሱር አብዱልቀኒ ፌስቡክ ገፅ

No comments:

Post a Comment