ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Sunday 11 November 2018

ተጠባቂው የማንቹኒያን ደርቢ ዛሬ ምሽት ይካሄዳል (ሰፊ የቡድን ዜናዎች)



ማንችስተር ዩናይትድ እና ማንችስተር ሲቲ ክለቦች ከሳምንቱ የቻምፒዮንስ ሊግ የድል መልስ በኋላ ዛሬ ምሽት በማንችስተር ከተማ የደርቢ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡

ዩናይትድ ከጨዋታ፣ ጨዋታ እየተሻሻለ ለመምጣቱ ምንም ጥያቄ የለውም የሚሉት የሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የአሸናፊነት ስነ ልቦናችን መልካም ደረጃ ላይ ስለሚገኝ ጨዋታውን እንቆጣጠረዋለን ብለዋል፡፡

በሁለቱ ክለቦች የማሸነፍ ታሪክ ማንችስተር ዩናይትድ የተሻለ ታሪክ አለው፡፡

ክለቡ እየተሻሻለ ስለመምጣቱ ጥርጥር የለኝም ያሉት የዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ አጀማመራችን በማሳመር በኩል ግን ችግር አንዳለባቸው አምነዋል፡፡

ያለባቸውን የቅንጅት ችግር ለመፍታት የበለጠ ስራ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

የማንችስተር ደርቢ ምሽት 1፡30 በኢትሃድ ስታዲዮም ይካሄዳል፡፡

የቡድን ዜናዎች What is the team news?

ሁለት ጨዋታዎች ካመለጡት በኃላ ወደ ልምምድ የተመለሰው ሮሚዮ ሉካኩ ሊሰለፍ ይችላል።

ሆኖም ደጋፊዎች ጆዜ ሞሪንዎ ቤልጂየማዊው አጥቂ ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ ተሽሎት ቢሆን እንኳን ጨዋታው ላይ እንዳያሰልፉት እየተማፀኑ ይገኛሉ።

አንቶኔ ቫሌንሺያ ምንም እንኳን ከጉዳቱ ቢመለስም በቱሪኑ ስኳድ ውስጥ መካተት አልቻለም ነበር። ዛሬ ምናልባት ሊሰለፍ ይችል ይሆናል።

ፖል ፖግባ በቡድኑ የሎውሪ ሆቴል ማረፊያ አርፍዶ ቡድኑን ተቀላቅሏል። ሆኖም ጆዜ ሞሪንዎ ከቡድኑ ስብስብ ውጪ ያደረጉበት የራሳቸው ልዩ ምክንያት እንዳላቸው ነው ሚታመነው።

ዲያጎ ዳሎት እና ፊል ጆንስ ሁለቱም ከጉዳታቸው በቅጡ ባለማገገማቸው አይሰለፉም።

ሲቲዎች በበኩላቸው ከቡድኑ ኮከብ ተጭዋች ኬቨን ዲ ብሪያንን ሳይዙ የመጀመሪያውን የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ ያደርጋሉ።

ሆኖም ማንቸስተር ሲቲዎች የቡድናቸው ኮከብ አማካይ ዲ ብርያን ከደረሰበት የጉልበት ጉዳት በፍጥነት አገግሞ በቅርብ ወደ ሜዳ እንደሚመለስላቸው የስፋ አድርገዋል። በዚህ ወር ላይ ወደ ሜዳ ይመለሳል ብለው ተስፋም ያደርጋሉ።
[Metro]

ዛሬ የሚደረገው ጨዋታ የማንቸስተር 177ተኛው ደርቢ በሁሉም ጨዋታ ይሆናል።  ማን.ዩናይትዶች ለ73 ጊዜ ሲያሸንፉ ሲቲዎች ለ51 ድል አድርገዋል። ለ52 ጊዜያት ያህል ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

የፕሪሚየር ሊጉን ብቻ ሪከርድ ካየን ዩናይትዶች ለ21 ሲያሸንፉ ሲቲዎች ደግሞ ለ42 ድል አድርገዋል። ለ13 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።


ማን. ሲቲን የሚገጥመው የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን ስብስብ : De Gea, Romero, Grant Young, Darmian, Lindelof, Bailly, Rojo, Jones, Smalling, Shaw Matic, Pereira,
Fred, McTominay, Herrera, Mata, Lingard, Fellaini Martial, Sanchez, Lukaku, Rashford (MEN ጋዜጣ)

የManchester City ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ባደረጓቸው ያለፉት 5ት ጨዋታዎች ላይ ያስመዘገቡት ውጤት : (ያለፉት 5 ጨዋታዎች ላይ - አሸ2 አቻ1 ተሸነፉ2)

♦ City 2-3 United
♦ United 1-2 City
♦ City 0-0 United
♦ United 1-2 City
♦ City 0-1 United

አሁን አፈትልኮ በወጣ ዜና ሮሚዮ ሉካኩ እና ፖል ፖግባ ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ተደርገዋል ሲሉ አንዳንድ ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ጋዜጠኞች ተናግረዋል።

What The Managers Said አሰልጣኞቹ ምን አሉ?

ጆዜ ሞሪንዎ ..

"ለማሸነፍ እንሞክራለን። ከሜዳችን ውጪ ሁለት ከባድ ጨዋታዎችን ከቼልሲ እና ከጁቬንቱስ ጋር አድርገናል። ጥሩ ውጤትም አስመዝግበናል። ምንም እንኳን ውጤቶቹ አጥጋቢ ናቸው ባይባሉም ተነሳሽነቱ የቡድን መንፈሱ አብሮን ነበር። ስለዚህ ለማሸነፍ ነው የምንሄደው እንሞክራለን ግን ማንቸስተር ሲቲ አሁን ያሉበት አቋም እና በጣም ትልቅ ቡድን መሆኑ እርግጥ ነው"

ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ አለቱ ዳኛ አንቶኒ ታይለር ...

"መሃል ዳኛው ስህተቶች መስራት የሚፈልጉ አይመስለኝም። በመላው አለም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾች ጨዋታውን በቀጥታ እንደሚመለከቱት ያውቃሉ፤ ስለዚህ በአለም ህዝብ ፊት ስህተት መስራት ይፈልጋሉ ብዬ አላስብም። ሆኖም የማን.ዩናይትድም ሆነ የማን.ሲቲ ደጋፊ ይሁኑ ያ ችግር ሊሆን አይችልም የፈለገውን ክለብ መደገፍ መብቱ ነው። ይሄ ችግር አይሆንም።"



No comments:

Post a Comment