ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Wednesday 28 November 2018

እሮብ ምሽት የወጡ አዳዲስ የዝውውር እና ሌሎችም ዜናዎች

ማንቸስተር ዩናይትዶች ክሪስቲያን ፑሊሲችን በ£50m የዝውውር ሂሳብ ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። የክለቡ ሊቀመንበር የሆኑት ኢድ ውድዋርድ ተጭዋቹ አሜሪካዊ መሆኑን ተከትሎ ትልቅ የገበያ እድል እንደሚፈጥርላቸውም አምነዋል። (ምንጭ: SPORTbild)




ዴቪድ ደ ሂያ ቀጣይ የእግር ኳስ ዘመኑንንም በማንቸስተር ዩናይትድ በመቆየት ማሳለፍ እንደሚፈልግ ለክለቡ ሰዎች አሳውቋቸዋል። ሆኖም አዲሱን ኮንትራት የሚፈርመው ሳምንታዊ ከ£300,000 በላይ ደሞዝ ከከፈሉት ብቻ መሆኑን ነግራቸዋል።   (ምንጭ: Standard)

.

ፈረንሳዊው ኢንተርናሽናል አማካይ ኦስማኔ ዴምቤሌይ ለባርሴሎና ሰዎች እንደነገራቸው ከሆነ በጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን የመልቀቅ ምንም ፍላጎት የለውም። የተጨዋቹ ስም ከአርሰናል ዝውውር ጋር በተደጋጋሚ ሲያያዝ መቆየቱ ይታወሳል።    (ምንጭ: ESPN)

.

የአርሰናሉ አለቃ አርሰን ዌንገር አዲሱ የባየር ሙኒክ አሰልጣኝ ለመሆን ዝግጁ እንደሆኑ ታወቀ።
(ምንጭ: Telegraph)

.

አያክሶች በአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ከሚፈለጉት የቡድናቸው ኮከብ ተጭዋቾች ማቲያስ ዲ ሊዥት(€65m) እና ፍራንክ ዲ ጆንግ(€75m) ዝውውር በድምሩ የ€140m ፓውንድ እንደሚያገኙ ተማምነዋል። ማን.ሲቲ እና ባርሴሎና የተችዋቾቹ ዋነኛ ፈላጊዎች ሲሆኑ ጁቬንቱስ እና ፒ.ኤስ.ጂዎች በበኩላቸው የ ዲ ሊዥት ፈላጊ ክለቦች ናቸው።
(ምንጭ: Mundo Deportivo)

.

ባርሴሎናዎች አዲስ የ£355m የስፓንሰርሺፕ ስምምነት በመፈራረም የስቴዲየማቸውን ስያሜ ካምፕ ኑ ለመቀየር ተቃርበዋል።   (ምንጭ: RAC1)

.

ማርኮ አሴንሲዎ ክለቡ ማድሪድ በክረምቱ ትልቅ ስም ያለው ተጭዋች የሚያዛውር ከሆነ ክለቡን ለመልቀቅ ተዘጋጅቷል። ጁቬንሱሶች የ22 አመቱን ስፔናዊ ለማዛወር የተሻለ እድል አላቸው።   (ምንጭ: Rai Sport)

.

ሪያል ማድሪዶች በክረምቱ የ€70m የዝውውር ሂሳብ የሚቀርብላቸው ከሆነ ኢስኮን ለመሸጥ ከውሳኔ ላይ ደርሰዋል። አርሰናሎች ተጭዋቹን ለማዛወር ከማድሪዶች ጋር ጠንከር ያለ ንግግር ማድረች ከወዲሁ ጀምረዋል።   (ምንጭ: Calciomercato)

.

የማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውር ኢላማ የሆነው ኢቫን ፔሪሲች ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መዛወር እንደሚፈልግ ተናገረ።

"በፕሪሚየር ሊጉ መጫዎት የሁልግዜም ህልሜ መሆኑን ከዚህ በፊት ደጋግሜ ተናግሬዋለሁ።" -  ሲል ኢንተር ሚላን ከቶተንሃም ጋር በቻምፒየንስ ሊጉ ከመጫወታቸው በፊት ተናግሯል።  (ምንጭ: Goal)

.

ጆኖዋዎች አጥቂያቸው ፒያቴክ ለማዛወር የሚፈልጉ ክለቦች ለዝውውር የ £44m ሂሳብ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል። ቼልሲ እና ናፖሊዎች የአጥቂው ዋነኞቹ  አንድ ፈላጊ ክለቦች ናቸው።   (ምንጭ: Tuttosport)

.

Official: አርሰናሎች ነገ በዩሮፓ ሊጉ ከሜዳቸው ውጪ በFK Vorskla Poltava ስቴዲየም ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በደህንነት ስጋት ምክንያት ወደ ኪየቩአ የOlimpiyskiy ስታዲየም መዛወሩ ተነግራል።  (ምንጭ: ChrisWheatley)

Tuesday 20 November 2018

አርሰናል ቼልሲ እና ሊቨርፑልን የተመለከቱ ትኩስ የዝውውር ዜናዎች



ትልቅ ዜና ለቼልሲ ደጋፊዎች! ንጎሎ ካንቴ ከሰማያዊዎቹ ጋር የሚያቆየውን የክለቡን ሪከርድ አዲስ ኮንትራት ለመፈረም ተዘጋጅቷል ..

ንጎሎ ካንቴ በቼልሲ ያለውን ኮንትራት ማደስ እንደሚፈልግ ፍቃደኝነቱን ጠቁሟል። ቼልሲዎች በበኩላቸው ለፈረንሳዊው አማካይ የክለቡ ሪከርድ የሆነ ሳምንታዊ የ£290,000 ደሞዝ ሊከፍሉት እንደሚፈልጉ Goal ተረድቻለሁ በሚል ዘግቧል።

የ27 አመቱ ኮከብ በስታምፎርድ ብሪጁ ክለብ ደስተኛ ሲሆን ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በ2015 ሌስተርን ተቀላቅሎ ከመጣ በኃላ ሊጉ ለርሱ አጨዋወት አመቺ ሆኖለታል።

ካንቴ አሁን በቼልሲ ሳምንታዊ £150,000 ደሞዝ የሚከፈለው ሲሆን ውሉ በ2021 የሚያበቃ ይሆናል። አማካዩ ክለቡ ቼልሲ ረጅም ኮንትራት ሊያስፈርማቸው ከሚፈልጋቸው ተጭዋቾች መሃል ከኤዲን ሃዛርድ ቀጥሎ ሁለተኛው ነው።


በሌላ ዜና የቦሩሲያ ዶርትመንዱ አማካይ ክሪስቲያን ፑሊሲች ቡንደስሊጋውን በመልቀቅ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ይመጣል። ሆኖም የቼልሲ እና የሊቨርፑል የዝውውር ኢላማ የሆነው ተጭዋች በጥር ሳይሆን በክረምቱ ዝውውር ወቅት ብቻ ዶርትመንድን እንደሚለቅ ተነግሯል። (ምንጭ: Daily Mirror)


GUNNING FORNALS አርሰናሎች ያለ አሮን ራምሴይ ህይወትን በኤምሬትስ ለማስቀጠል ተዘጋጅተዋል።

እናም ኡናይ ኤምሬ የቪያሪያሉን አማካይ ፓብሎ ፎርናሌስን ለማዛወርና የዌልሳዊው ምትክ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል። ተጭዋቹ በዚህ አመት በላ ሊጋው ያገባት ጎል Goal Of The Season በሚል እጩ በመሆን ሊመረጥለት ችሏል።

አርሰናሎችም የስፔናዊው ተጭዋች ውል ማፍረሻ ሂሳብ የ£17.8 ሚሊዮን በመክፈል በጥር የዝውውር መስኮት ሊያስፈርሙት ተዘጋጅተዋል።

Monday 19 November 2018

ሰኞ ምሽት የወጡ በርካታ አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች

ማንቸስተር ዩናይትዶች የንጎሎ ካንቴ ወኪል ጋር ቀርበው ንግግር ጀምረዋል። ተጭዋቹን ሳይጠበቅ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ወደ ኦልትራፎርድ። ለማዛወር ወጥነዋል።  (ምንጮች፦ M.E.N,Star እና Express)



የሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ አሜሪካዊውን የዶርትመንድ አማካይ ክርስቲያን ፑሊሲች በ £70 ሚሊዮን የዝውውር ዋጋ ለማዛወር በሚደረገው ፉክክር ላይ ቼልሲን ተቀላቅለዋል።  (ምንጭ፦ Sunday Mirror)



የአርሰናሉ አማካይ አሮን ራምሴይ ወደ ጁቬንቱስ ለመዛወር የሚስማማ ከሆነ አመታዊ የ£10.4 ሚሊዮን ደሞዝ ሊከፍሉት ፈቅደዋል።  (ምንጭ፦ Sun on Sunday)



ካስካሪኖ : “ምን አለ በሉኝ! ጎሜዝ ለቀጣዩ አስር አመታት የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ቀዳሚው ተመራጭ መሃል ተከላካይ ይሆናል። አሰልጣኙ ቡድኑን በሚመርጥበት ግዜ በቀዳሚነት የሚያስቀምጠው እርሱን ይሆናል" - ሲል ተጭዋቹ ከፊቱ ብሩህ ተስፋ እንዳለው መስክሮአል።
(ምንጭ፦ liverpoolfc)



ጂኒ ዊናልድረም: “ሰዎች ብዙ ግዜ እኔ የአማካይ ስፍራ ተጭዋች እንዳልሆንኩ ይልቅ የክንፍ መስመር ተጭዋች እንደሆንኩ ሊነግሩኝ ይፈልጋሉ።"

"በርካታ አሰልጣኞች 'በክንፍ መስመር ላይ ብትጫወት ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግህ ልዩ ክህሎት አለህ' እያሉ የሚመክሩኝ አሰልጣኞች ብዙ አሉ" - ሲል የርገን ክሎፕ በክንፍ መስመር እንዲሞክሩት እግረ መንገዱን ጠቁሟል።
(ምንጭ፦ liverpoolfc)



ማንቸስተር ዩናይትዶች የዌስትሃሙን ዲክላን ሪሴ ለማዛወር ሙከራ ላይ ናቸው ሆኖም ለተጭዋቹ ዝውውር ከአርሰናል እና ሊቨርፑል ፉክክር ገጥሞአቸዋል።  (Source: Daily Express)



ሪያል ማድሪዶች በጥር የዝውውር መስኮት ላይ አጥቂ ለማዛወር ወደ ገበያው ይወጣሉ። ሉስ ብላንኮዎቹ በጋሬዝ ቤል እና ካሪም ቤንዜማ ላይ የነበራቸው እምነት ተሟጧል።  (Source: Sport)



ማንቸስተር ዩናይትዶች የሮማውን ሎሬንዞ ፔሌግሪኒ ደሞዝ እጥፍ በማድረግ ለማዛወር ሙከራ እያደረጉ ነው። ተጭዋቹ በ£26 ሚሊዮን የዝውውር ሂሳብ ወደ ኦልትራፎርድ ሊያመራ ይችላል የሚሉ ዘገቦች ተበራክተዋል።  (ምንጭ፦ Corriere dello Sport)



ኤሲ ሚላኖች ስፔናዊውን የቼልሲ አማካይ ሴስክ ፋቤጋዝ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ስለሚያዛውሩበት ሁኔታ ከወዲሁ ንግግር ማድረግ ጀምረዋል።   (ምንጭ፦ Calciomercato)



ሪስ ኔልሰን ሆፌንሄምን በውሰት ለመቀላቀል ስለመወሰኑ: “እኔ ሁሌም ያለኝን አቅም በማውጣት ምርጥ ተጭዋች የመሆን ህልም አለኝ። ገና 18 አመቴ ላይ ብሆንም ወደ ቡንደስሊጋው ብዛወር ጥሩ ፈተና ሊሆነኝ እንደሚችል አውቃለሁ። ወደዛ መዛወሬ የተሻልኩ ተጭዋች እንደሙያደርገኝ አምን ነበር። ወደ ጀርመን መሄዴ በቀጣይ የእግርኳስ ህይወቴም ከሜዳም ውጪ እንደሰው የተሻልኩ እንደምሆን ተስፋዬ ነው።"



ናፖሊዎች ምንም እንኳን በውሰት ያዛወሩት ግብ ጠባቂያቸው ዴቪድ ኦስፒና ውሉ ላይ እንደሰፈረው 'በ30 ጨዋታዎች ላይ ሆኖ ከተሰለፈ ዝውውሩ ቋሚ ይሆናል' የሚለው አንቀፅ ሳያስገድዳቸው ግብ ጠባቂውን በክረምት ሊያስፈርሙት ከውሳኔ ላይ ደርሰዋል።   (ምንጭ፦ La Repubblica)



ሮበርት ሎዋንዶውስኪ በዚህ የውድድር አመት በሁሉም ውድድሮች ላይ ባደረጋቸው 16 ጨዋታዎች ላይ ያስመዘገበው የጎል መጠን 15 ሲሆን 5 ጎል የሆኑ ኳሶችን አቀብላል። በየ72 ደቂቃ አንድ ጎል ላይ በማግባት አሊያም በማቀበል ተሳትፎ አድርጎአል።
(ምንጭ፦ iMiaSanMia)



በበርካታ ታላላቅ ክለቦች አይን ውስጥ የገባው ሆላንዳዊ አማካይ ማቲያስ ዲ ሊዥት ሆላንድ እና ጀርመን ጨዋታ ወቅት ጋዜጣዊ መግለጫ በሚሰትበት ወቅት ባየር ሚኒኮች ሊያስፈርሙት ጥያቄ ስለማቅረባቸው ቢጠይቁትም የሆላንድ ቡድን ፕሬስ ኦፊሰር የሆኑት ግለሰብ ግን መልስ እንዲሰጥ አልፈቀዱለትም፤ ምክንያቱም ጋዜጣዊ መግለጫው የዝውውር ሁኔታ ቃለ ምልልስ አይደለም ብለዋል።
(ምንጭ፦ Kicker)



ባየር ሙኒኮች በቀጣይ ክረምት የዝውውር መስኮት ላይ ቡድናቸውን በአዲስ ስብስብ ለማጠናከር ያቀዱ ሲሆን ሁለት የክንፍ መስመር ተጭዋቾችን ለማዛወር አቅደዋል።  (ምንጭ፦ Kicker)



የፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን ካምፕ እንዳረጋገጠው ከሆነ የማን.ሲቲው በርናንዶ ሲልቫ የአካል ብቃት ችግር ስላለበት ዛሬ ከቡድኑ ጋር ልምምድ አላደረገም። ቡድኑ ነገ ከፖላንድ ጋር በሚያደርገው የUNL ጨዋታ ላይም አይሰለፍም።  (ምንጭ፦ CityWatch)



ሪያል ማድሪዶች የ21 አመቱን የአያክስ አማካይ ፍራንክ ዲ ጆንግ ለማዛወር በሚደረገው ፉክክር ላይ ዘግይተውም ቢሆን ተቀላቅለዋል። ሆኖም የረፈደባቸው ይመስላል። የማን.ሲቲው ቲኪ ብምግሪስታን ለበርካታ ጊዜያት ያህል ከክለቡ አያክስ እና ከተጭዋቹ ጋር ተገናኝተው ዝውውሩ ላይ ከተፎካካሪዎቻቸው ቀድመው ተገኝተዋል። የባርሴሎናዎችም በተጭዋቹ ዝውውር ድርድሩ ላይ ቀደም በማለት ገፍተው የተንቀሳቀሱ ሌላኛው ክለብ ናቸው።  (ምንጭ፦ SPORT)



ኤሲ ሚላኖች በውሰት ከለንደኑ ክለብ ቼልሲ ያዛወሩትን አማካይ ቲሞው ባካዮኮ ውል ወደ ቄሚ ዝውውር ለመቀየር ፍላጎት ያሳደሩ ቢሆንም ለዝውውሩ ከ £22 ሚሊዮን በላይ ለሰማያዊዎቹ መክፈል አይፈልጉም።  (ምንጭ፦ 90min)



ሉዊስ ሄነሪኬ በዴቪድ ደ ሂያ ላይ ያላቸው እምነትና ትግስት በመሟጠጡ በእርሱ ምትክ የቼልሲውን ግብ ጠባቂ የስፔን ብሄራዊ ቡድን ቁጥር1 ተመራጭ ለማድረግ ከውሳኔ ላይ ደርሰዋል።  (ምንጭ፦ 90min)



ማንቸስተር ዩናይትዶች የናፖሊውን መሃል ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ ለማዛወር የ€90 ሚሊዮን ወይም £80 ሚሊዮን ሂሳብ ለክለቡ አቅርበዋል።
(ምንጭ፦ Metro)

Sunday 18 November 2018

ፖል ፖግባ እና ሊዮኔል ሜሲ በዱባይ ለምን ታዩ?



የMANCHESTER UNITED ደጋፊዎች ፖል ፖግባን ከሊዮኔል ሜሲ ጋር መታየቱ ተጭዋቹ ወደ ባርሴሎና እንዲዛወር ሊያማልለው ይችላል የሚል ስጋት ገብቷቸዋል።

ፈረንሳዊው በዱባይ በሚገኘው የSalt Bae 's plush steak house ከአርጀንቲናዊው ኮከብ ጋር ሻይ ቡና እያለ ሲያወጋ ታይቷል።

ፖግባ በማንቸተር ዩናይትድ ያለው ቆይታ ባልተረጋገጠበት በዚህ ሰአት ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ተቀምጦ ማውጋቱ ደጋፊዎቹን አልጣመም።

ነውጠኛው ወኪል ሱፐር ኤጀንት ሚኖ ራዮላ በ£89 million የዝውውር ሂሳብ ወደ ኦልትራፎርዱ ክለብ ያዛወረውን አማካይ ወደ ባርሶሎና ለማዛወር ጠንክሮ በመስራት ላይ ይገኛል።

በተለይ ተጭዋቹ ከጆዜ ሞሪንዎ ጋር ያለው መጥፎ የሚባል የእርስ በእርስ ግንኙነት የካታላኑ ግዙፍ ክለብ በጥር የዝውውር መስኮት ሊያዛውሩት ጥያቄ እንዲያቀርቡ ይገፋፋቸዋል ተብሏል። ሆኖም ዩናይትዶች ለዝውውሩ የ£200 million ሂሳብ ከቀረበላቸው ሊመለከቱት ዝግጁ ናቸው።

እናም የማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች እንደሚያምኑት ከሆነ በተለይ ሁለቱ ኮከቦች በአረቧ ውብ ከተማ አንድ ላይ መታየታቸው ጉዳዩን ይበልጥ ሊያፋጥነው ይችላል ብለው ሰግተዋል።

አንድ ደጋፊ እንዳለው ከሆነ: "የሚመስለው ሊዮኔል ሜሲ ፖል ፖግባ ወደ ባርሴሎና እንዲዛወር እያሳመነው ይመስላል"

ሌላኛው ደጋፊ ደግሞ እንዳለው: "ንግግራቸው ሜሲ ወደ ኦልትራፎርድ ሳይሆን ፖግባ ወደ ካምፕኑ እንዲመጣ ለማሳመን ነው"

ፖግባ በእለቱ ነጭ ጥያቄ ያስነሳ ወጣ ያለ አለባበስ ጥቁር ጣል ያደረገበት ነጭ ቲሸርት እና ነጭ ጅንስ ልብስ ለብሶ ታይቷል።

እንዲሁም ተጭዋቹ አይነት ራሱ ላይ ሻሽ በማሰር የRichard Mille Flyback አለባበስ የነበረው ሲሆን እጁ ላይ የ£124,611 ዋጋ የሚያወጣ እጅግ ውድ ሰአት አድርጎ ነበር።

ተጭዋቹ በደረሰበት ጉዳት ሳቢያ የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን በሆላንድ በደረሰባት ሽንፈት ላይ መሰለፍ ባለመቻሉ ነው በዱባይ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ሲዝናና የታየው።

Friday 16 November 2018

ፖል ስኮልስ ያ ምሽት፣ ያ ማሊያ (የአሸናፊውና ተሸናፊው ወግ)



(በመንሱር አብዱልቀኒ)
"ስለዚያ የፍፃሜ ጨዋታ ሳስብ፣ የሚታወሰኝ የመጨረሻው 30 ደቂቃ ነበር" ይላል ኤሪክ አቢዳል። ስለ2011ዱ ቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ እያወራ ነው። ገና ሊጠናቀቅ ግማሽ ሰዓት እየቀረው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች መሸነፋቸውን አምነው ተቀበሉ። የባርሴሎናን የምሽቱን ኃያልነት ምንም አይነት ጥረት ሊቀለብሰው እንደማይችል ዩናይትዶች ቀድመው ተረዱ። እንደው ቦክስ አይደል ፎጣ አይወረወር ነገር!

የባርሳ ልጆች ይጫወቱታል። በእግሮቻቸው ቅብብል ሜዳውን በአይነ ህሊናዊ መስመሮች ይሸረካክቱታል፣ ያለ እጅ ንክኪ ይከፋፍሉታል፣ ያለ ቢላዋ ይበልቱታል። እኒያ ታላቅ ጀግና ሰር አሌክው ፈርጉሰን እንኳን ዓይኖቻቸው በካታላኑ ጥበባዊ ትርምስ ቦዘው ስልት የተሟጠጠበት የጦር መሪ መስለዋል።

ኢኒዬሽታ ለቻቪ…፣ ቻቪ ለሜሲ ይሰጠዋል።… ከዚያ ቡስኬትስ ይመጣና ይቀበላል፣ መልሶ ያቀብላል። ፒም-ፓም…፣ ፒም-ፓም…፣ ፒም-ፓም…።

"እንግሊዛዊያኑ ተጫዋቾች ተማረሩ" አቢዳል ስለመጨረሻው 30 ደቂቃ ትውስታውን ቀጠለ።

"ዌምብሌይን ወደ ግዙፍ ሮንዶ (መሐል ባልገባ) ስለቀየርንባቸው ብስጭት ገባቸው። ሊያቆሙን አቃታቸው። አቅመ ቢስ ሆኑ።

"የብልግና ቃላትን ጨማምረው የብስጭታቸውን ያህል ይናገራሉ። ምን ቀራቸው…፣ ከፀሃይ በታች ባለ ስድብ ሁሉ ይጮሃሉ። ይገርማል። ከቡድን ጓደኞቼ አንዳንዶቹ ተጫዋቾቹ በቋንቋ ምክንያት ምን እያሉ እንደሆነ አልገባቸውም ነበር። እኔ ግን ተረድቼዋለሁ። "…በቃኮ! አልቆልናል፣ ሞተናልኮ። በቃ! ለምን አይበቃችሁም?" ሲሉን ጨዋታው ሊያልቅ ገና 25 ደቂቃ ይቀረው ነበር።

ቻቪ፣ ኢኒዬሽታ፣ ቡስኬትስ ቀጠሉ። ፒም-ፓም…፣ ፒም-ፓም…፣ ፒም-ፓም…።

አቢዳል እንከን የለሽ የቡድን ስራ፣ ወደ ውብ ጨዋታ ሲቀየር እያስተዋለና ራሱም እየተጫወተ ነበር። በህልም ዓለም የሚታሰበው ሁሉ እየሆነ ነው። ለእርሱ ልዩ፣ ከልዩም ልዩ ጨዋታ ነበር።

አቢዳል በመጀመሪያው አሰላለፍ ውስጥ ይካተታል ብሎ የገመተ አልነበረም። በጉበቱ ላይ የካንሰር ዕጢ መገኘቱ ከተነገረ ገና ሁለት ወር መሆኑ ነው። መጥፎው ዜና በተሰማ ማግስት ከጨዋታ በፊት መልበሻ ቤት ገብቶ ጓደኞቹን አበረታቷል። ከሁለት ቀን በኋላ ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል ሲገባ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ለተጨዋች ጓደኞቹ "ጉበቱን የሚሰጠኝ" እያለ ይቀልድባቸው ነበር። ሜይ 28 ደግሞ በዌምብሌይ ለፍፃሜው ተሰለፈ።

"ልዩ የሆነብኝ ፑዮልና ቻቪ ዋንጫውን እንዳነሳ ዕድል ስለሰጡኝ ወይም በዌምብሌይ የሞቀ ድባብ ምክንያት እንዳይመስላችሁ። በፉትቦሉ ጥራት እንጂ…" ይላል።

ያኔ አንድሬስ ኢኒዬሽታ በችሎታው ተራራ ጫፍ ላይ ነበር። ዌምብሌይ ከጉዳት ነፃ የሆነበት የመጀመሪያው የፍጻሜ ጨዋታ ሆነለት። እንደ እምቦሳ እየፈነጠዘ፣ እንደ ልባም ፈረስ እየጎደፈረ፣ ኳሷን በተዓምራዊ ፍጥነትና ጥበብ ወደፈለገው ቦታ እየላካት ያዛታል።

የኦርኬስትራው አካል ቢሆንም አቢዳል ተመልካችም ጭምር ነበር። ካታላኑ በኳስ ቅብብል ያለድምፅ ያዜማሉ። ጥበብ በኢኒዬሽታ ያማረ መልኳን ስትገልጥ ፈረንሳዊው ተከላካይ እየታዘበ ይደመማል።

ቻቪ የአቢዳልን ትውስታ ያጠናክራል።

"…አዎን! አቢ እውነቱን ነው። ሩኒ ወደ እኔ መጣና አነጋገረኝ። 'አይበቃችሁም እንዴ? በቃ አሸንፋችኋልኮ' አለኝ። ሰዓቱ ግን 80ኛ ደቂቃ ገደማ ነበር። 'በቃ ኳሱን ማንሸራሸራችሁ ይብቃ  ' ይለኝ ነበር።…"

አያልቅ የለ የፍፃሜው ፊሽካ ተሰማ። ፔፕ ጋርዲዮላና ልጆቹ አሳምነው 3ለ1 አሸነፉ። ባርሳ የአውሮፓ ሻምፒዮን ተባለ።

ካርለስ ፑዮል የአምበልነቱን ጥብጣብ በፍቃደኝነት በአቢዳል ክንድ ላይ አሰረው። ከካንሰር ህመም በህክምና ጥበብ የተመለሰው አቢ ዋንጫውን በክብር ሲያነሳ ስኮልስ ባለ 18 ቁጥሩ ነጭና ቀዩን ማሊያ ለብሶ ትዕይንቱን ፈዞ ይመለከታል። በእውነት ይህን ያህል ተበልጠን እንሸነፋለን ብሎ አልገመተም ነበር።

በዚያች ምሽት፣ በለንደን የእግር ኳስ ካቴድራል ተሸናፊው ሰራዊት ዩናይትድ ቢሆንም፣ የድል አድራጊዎቹን ልብ ቀድሞ በአድናቆት ያቀለጠ ተጫዋች ከዚያ ወገን ውስጥ አለ። የባርሳ ከዋክብት ከፖል ስኮልስ ጋር መጫወትን ሲመኙ ኖረዋል። ቻቪ እጅጉን ያደንቀዋል፣ ኢኒዬሽታ "ምነው ከእርሱ ጋር በአንድ ቡድን ውስጥ ባጫወተኝ" እያለ አልሟል።

የእርሱን ማሊያ "እኔ እወስድ፣ እኔ እወስድ" እያሉ ሲጨቃጨቁበት አቢዳል ሰምቷል። በዚያ ምሽት አድናቂዎቹ በድል ደስታ ሰክረው ሳለ ስኮልስ ግን ከእነ ማሊያው ቆሞ የሽንፈቱን ራስ ምታት ያዳምጥ ነበር።

ተሸናፊው የአሸናፊዎቹን ፓርቲ እየታዘበ የዌምብሌይ ሜዳ አልበቃህ ብሎት፣ በእግሩ የነካው ሁሉ ወርቅ ሲሆንለት ያየው አንድሬስ ወደ እርሱ መጥቶ ማሊያውን ሲጠይቀው ሳይደነቅ አልቀረም።
                             
… ኢኒዬሽታ በተወለደበት ፎንቴያልቢያ የወይን እርሻ ባለቤት ነው። ከእርሻውም ጎን የወይን ጠጅ መጥመቂያ ፋብሪካ አለው። እዚያው መኖሪያ ቤቱን ገንብቷል። ከቤቱ ጓዳዎች በአንዱ፣ በወይን ጠጅ ማከማቻ ክፍል ግድግዳ ላይ በመስተዋት ፍሬም ውስጥ አንድ ብርቅዬ ማሊያ በክብር ተሰቅሏል። ፖል ስኮልስ በዌምብሌይዋ ምሽት የለበሰው ያ ማሊያ።

(ምንጭ፦ መንሱር አብዱልቀኒ Facebook ገፅ)
ምስል ቅንብር እና አዘጋጅ - መንግስቱ ደሳለኝ

Thursday 15 November 2018

Moments: ጆዜ ሞሪንዎ ያቺን ሰአት (በመንሱር አብዱልቀኒ)

ሞውሪንሆ ያቺን ሰዓት

በሪያል ማድሪድ መልበሻ ቤት የበግ ለምድ የለበሰ ተኩላ አለ። ጆዜ ሞውሪንሆ አድብቶ የሚያስጠቃቸውን የዚህን ፍልፈል ማንነት አላወቁም። ዕረፍት ነሳቸው። የመልበሻ ክፍሉን ድብቅ መረጃዎች ለጋዜጦች የሚሰጠው ማነው? ጆዜ ቆረጡ። "መጋለጥ አለበት" አሉ።

የጋዜጦችን ዕለታዊ ወሬ ሰብስበው በየማለዳው ጠረጴዛቸው ላይ የሚያስቀምጡላቸውን ሰዎች በወኪላቸው ዦርጌ ሜንዴዝ ኩባንያ "ጄስቲፊዩት" በኩል ቀጠሩ። ሰዎቹ ሚድያ የተነፈሰውን ሁሉ… እንደወረደም ይሁን ተብራርቶና ተተንትኖ ለአለቃቸው ያቀርባሉ።

የጆዜ ቀን ዘወትር ከማለዳው 2:00 ሰዓት ላይ ይጀምራል። በልምምድ ማዕከሉ በሚገኘው ቢሯቸው የጋዜጣ ላይ ዘገባዎችን፣ አስተያየቶችንና የቲቪ ፊልሞችን በማየት አይናቸውን ይገልጣሉ። ሚድያው የቡድኑን ምስጢር ሁሉ ይዞ መውጣቱን ቀጥሏል። ጆዜ አንጀታቸው እያረረ መልስ ያላገኙለትን ጥያቄ ይጠይቃሉ። ፍልፈሉ ማነው?

የመረጃውን ጥራት ሲመለከቱት ደግሞ በቡድኑ አባላት መካከል ባሉ ሰዎች በኩል የሚወጣ ምስጢር አልመስልህ አላቸው። የሆነ…፣ የተደበቀ ድምፅ መቅጃ ሳይኖር እንደማይቀር ጠረጠሩ። በድብቅ ንግግሮቻቸውን የሚያደምጥ ካልሆነ በስተቀር ያቦኩት ሳይጋገር ለአደባባይ ሊበቃ አይችልም።

ቡድኑ ከጨዋታ በፊት በሚያርፍበት ሆቴል ውስጥ የሚሰሩ ሁለት የፅዳት ሰራተኞች ድብቅ መቅረፀ ድምፅ እንዲፈልጉ አዘዟቸው። ሼራተን ሚራሲዬራ ተበረበረ፣ በየጥጋጥጉ ተፈተሸ። ምንም አልተገኘም።

ጆዜ ጦፉ። ቀጣዩ ጨዋታ ኤልክላሲኮ ስለሆነ ደም፣ ደም ሸቷቸዋል። ሲብስባቸው ለክለቡ ከፍተኛ አለቆች የተጫዋቾቻቸውንና ሰራተኞቻቸውን የስልክ ምልልስ እንዲጠልፉና የሚያወሩትን እንዲቆጣጠሩ ጠየቋቸው። አንዳንድ ተጫዋቾች ነገሩ በማስጠንቀቂያ መልክ ተነገራቸው። በእጅ ስልኮቻቸው በኩል የሚያወሩትን ነገር ይዘትና የሚያነጋግሩትን ሰው ማንነት እንዲመርጡ ተመከሩ።

አፕሪል 16 ቀን 2011፣ በቤርናቢዩ ከባርሳ ጋር ከመጫወታቸው ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ ማርካ ጋዜጣ "ዛሬ ፔፔ ይሰለፋል፣  ኬዲራ እና አሎንሶ ያጣምሩታል" ሲል ሜሱት ኦዚል ተጠባባቂ እንደሚሆን ዘገበ። እንደገና ምስጢር አፈተለከ።

ሰዓቱ ደርሶ ቡድኑ ሊሟሟቅ ሲወጣ ተጫዋቾች በሜዳው ላይ ያልተለመደ ነገር አስተዋሉ። ሳሩ ከወትሮው ይልቅ ረዝሟል። በቅጡ አልታጨደም። ረጅምና ደረቅ ነው። የባርሳን የኳስ ሂደት ለማወክና ለማዘግየት መሆኑ ግልፅ ሆነላቸው።

በጨዋታው ማድሪድ በትዕዛዝና በኃይል መከላከልን መረጦ አፈገፈገ። ባርሳዎች ደግሞ ኳሱን አብዝተው በእግራቸው ስር አቆዩ። ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶች ተሰጡና ሁለቱም ተቆጠሩ። አንድ በሮናልዶ፣ አንድ በሜሲ። የመጨረሻ ውጤት? ... 1- 1።

ከዚህ ጨዋታ በፊት ከጋርዲዮላ ባርሳ ጋር በተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች 0-2 እና 2-6 ተሸንፈዋልና አሁን ባያሸንፉም የቤርናቢዩ ደጋፊዎች እፎይታን አገኙ። አቻው ውጤት ግን የሪያልን የዋንጫ እድል የሚያጠብ ነበር።

ጆዜ ተጫዋቾች በመልበሻ ቤት እስኪሰባሰቡ ጠብቀው ማንባረቅ ጀመሩ። ስድብ አዘል የስፓኒሽ ቃላት እንደ በረዶ ውሽንፍር በተጫዋቾቹ ላይ ዘነቡ።

"ከሃዲዎች ናችሁ! ከዳተኞች! የማትታመኑ ናችሁ! ስለቡድኑ አሰላለፍ ለማንም እንዳትናገሩ ነግሬያችሁ ነበር። እናንተ ግን ከእኔ ወገን እንዳልሆናችሁ አሳያችሁ። የውሻ ልጅ ሁሉ! ብቸኛው ጓደኛዬ ግራኔሮ ብቻ ነበር። አሁን ግን እርሱንም ማመን እየቸገረኝ ነው። ብቻዬን ተዋችሁኝ። ከገጠሙኝ ቡድኖች ሁሉ እንደዚህ ከዳተኞች የበዙበት ስብስብ አይቼ አላውቅም…።"

የአሰልጣኙ ቁጣ ማለቁን ሳይጠብቅ ኢኬር ካሲያስ ጥሏቸው ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ገባ። አንዳንዶቹም ተከተሉት። ንዴት እንደ ጉሽ ጠላ አናታቸው ላይ የወጣባቸው አሰልጣኝ በአፍታ እብደት አጠገባቸው ያገኙትን ሬድ ቡል በካልቾ ጠለዙት። ቆርቆሮው በኃይል በሮ ከግድግዳው ጋር ሲላተም እግረ መንገዱን በውስጡ የያዘውን ፈሳሽ በአቅራቢያው በሚገኙ ተጫዋቾች ፊት ላይ ረጨው።

ያኔ ጆዜ በንዴት በግነውና ተጨማሪ ስድቦችን አስከትለው፣ እየተቆጡ በመልበሻ ቤቱ ወለል ላይ በጉልበቶቻቸው ተንበረከኩ። ሲነሱም በዓይናቸው ስር እምባቸውን ይጠራርጉ ነበር። ዛቻ አስከትለው ለቁጣቸው ማሳረጊያ አበጁለት።

"ግዴለም! ለ[ፍሎሬንቲኖ] ፔሬዝ እነግረዋለሁ። ራሱ ወሬ አቀባዩን ፈልጎ ያጋልጠው። በቪዬትናም ብሆን ኖሮ፣ በጓደኛችሁ ላይ እንዲህ ስትቀልዱ ብመለከት ሽጉጤን መዝዤ በደፋኋችሁ ነበር…።"

Wednesday 14 November 2018

ማርኮ አርናቶቪች ማን.ዩናይትድን በጥር ሊቀላቀል እንደሚችል ወኪሉ ፍንጭ ሰጠ

አርናቶቪች እንዳለው ከሆነ ዌስትሃምን በጥር የዝውውር መስኮት ላይ መልቀቅ ይፈልጋል።

አዉስትሪያዊዉ ኮከብ ከምርጥ ተጭዋቾች ጎን መጫወት እፈልልለሁ ያለ ሲሆን ወኪሉ እና ወንድሙ የሆነው ዳንዥል እንዳለው ከሆነ ቀጣይ ሊዛወር የሚፈልግበት ክለብ የተሻለ ትልቅ ቡድን ነው።


MARKO ARNAUTOVIC ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ በመናገር የክለቡን ደጋፊዎች አስደንግጧል።

የዌስትሃሙ አንበል ባለፈው ሲዝን ላይ የቡድኑ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ የጨረሰ ሲሆን ቡድኑ ወደ ታችኛው ዲቪዚዮን እንዳይወርድ ያድነናል ብለው ተፋ ያደረጉበት ተጭዋቻቸውም ነበር።

ሆኖም የቀድሞው የስቶክ ሲቲው ሰው ኮከብ በከፍተኛ ደረጃ መጫወት እፈልጋለሁ ብሏል። ወንድሙ እና ወኪሉ ዳንዥል ለአውስትሪያው ጋዜጣ Kurier እንዳለው ከሆነም ..

"አሁን ቀጣይ ክለብ ላይ ለመጫወት ተዘጋጅቷል።"

አርናቶቪች በበኩሉ ..
"አሁን የ29 አመት ሰው ነኝ። ይሄ ጥር እድሜዬ ነው።
ከምርጥ ተጭዋቾች ጋር መፎካከር ራሴን ማየት መፈለጌ ኖርማል ነው።

"ሆኖም በዚህ ጉዳይ ላይ ወንድሜን በጣም አምነዋለሁ።"

የአርናቶቪች ወንድም ተጭዋቹ በ2017 ላይ ከስቶክ ሲቲ ወደ መዶሻዎቹ በ£25 million የዝውውር ሂሳብ እንዲዛወር ያደረገ ወኪሉም ነው። እናም አሁንም ለተጭዋቹ ገዢ ክለብ ለመፈለግና ለመደራደር ቢዚ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ለአውስትሪያው ጋዜጣ እንዳለው ከሆነ ..

"አሁን ተጭዋቹ በፕሪሚየር ሊጉ የመጫወት በቂ ልምድ አዳብሯል። ይሄ ሊግ ደሞ ምርጥ ተጭዋቾች የሚገኙበት ሊግ ነው። ሆኖም ማርኮን ለመሰለ ጎበዝ ተጭዋች ደግሞ በዌስትሃም ብቻ መጫወት ትልቁ ግብ አይደለም።

"የዌስትሃም ቡድን አንዱ ትልቁ አካል እንደሆነ ይታወቃል። ሆኖም የተሻለ ክለብ መቀየሩ የሚቻል ነገር ነው።

"ለትልቅ ክለብ መጫወት አለበት። ማርኮ ለቀጣይ ስቴፑ አሁን ዝግጁ ሆኑአል። እንደርሱ አይነት ተጫዋች ለመውረድ በሚታገል ቡድን ውስጥ መጫወት የለበትም። ከፍ ባሉ ደረጃዎች ባላቸው ውድድሮችም ላይ መሳተፍ አለበት።

"ማርኮ ለዌስትሃም መጫወቱን ወዶታል። ክለቡን።እና ደጋፊዎቹን ከልቡ ይወዳል።"

የማርኮ አርናቶቪች የእግርኳስ ህይወት ስታቶች..

• ለትዌንቴ ክለብ : 59 appearances - 14 goals
• ለኢንተር ሚላን : 3 appearances - 0 goals
• ለወርደር ብሬመን : 84 appearances - 16 goals
• ለስቶክ : 145 appearances - 26 goals
• ለዌስትሃም : 46 appearances - 16 goals

"በጥር ሊለቅ የሚችልበት አማራጮች አሉን። እንደውም በክረምቱ ክለቡን ለመልቀቅ በጣም በጣም ተቃርቦ ነበር"

ማንቸስተር ዩናይትዶች የ29 አመቱን ተጭዋች ያስፈርማሉ በሚል በክረምቱ በተደጋጋሚ ስማቸው ሲነሳ ቆይቷል። እናም አሁንም በድጋሚ በጥር ወር ፊርማውን ለማግኘት እንደሚንቀሳቀሱ ይጠበቃል።