ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Tuesday 13 November 2018

አሁን የወጡ ተጨማሪ አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች



➧  ማንቸስተር ዩናይትዶች ምንም እንኳን አሌክሲስ ሳንቼዝ ክለቡን የመልቀቅ ፍላጎት ቢኖረውም እና እነሱ መሸጥ ቢፈልጉም በረብጣ ሳምንታዊ ደሞዙ ምክንያት ገዢ ክለብ ላናገኝ እንችላለን የሚል ስጋት ገብቷቸዋል።  (Source: Daily Telegraph)

.

➧  የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች የ Brexit Deal ላይ ሊወያዩ ነው። ውይይቱ ፍሬያማ ሆኖ ተቀባይነትን የሚያገኝ ከሆነ በእያንዳንዱ ቡድን ውስጥ የሚጫወቱ የውጭ ሃገራት ቡድኖች አሁን ካሉበት 17 ወደ 12 ይወርዳል። ይሄ ማለት ደግሞ ሃገር በቀል ተጭዋቾችን ቁጥር ወደ 13 ከፍ ያደርጋል።  [Sky Sports]

.

➧  ኬቨን ዲ ብሪያን ከተባለለት ጊዜ በፍጥነት አገግምም ወደ ሜዳ ሊመለስ ነው። ተጭዋቹ የቀድሞ ክለቡን ቼልሲ በዲሴምበር ወር ለመግጠም ብቁ ይሆናል። ዲ ብርያን ባሁን ሰአት ዲሰምበር 4 ላይ ዋትፎርድ ጨዋታ ላይ ለመመለስ ግብ አድርጎ እየሰራ ይገኛል።  [Guardian]

.

➧  ጆዜ ሞሪንዎ ሁለቱን ተከላካዮቻቸውን ማርኮስ ሮሆ እና ኤሪክ ቤይሊን በጥር የዝውውር መስኮት ላይ በመሸጥ ከሽያጩ በሚያገኙት ገንዠብ ላይ ጨምረው ከቶቢ አልደርዌልድ እና ሚላን ክሪኒያር አንዳቸውን ለማስፈረም አስበዋል።
(Source: Daily Telegraph)

.

➧  ምንም እንኳን በፊፋ ፋይናንሺያል ፋየር ፕላይ ህግ ጥሰት ምርመራ እየተደረገባቸዉ ቢሆንም ማንቸስተር ሲቲዎች የአያክሱን አማካይ ፍራንክ ዲ ጆንግን በ£50 ሚሊዮን የዝውውር ሂሳብ ለማዛወር አሁንም ሙከራ ላይ ናቸው።   (Source: Sun Sport)

.

➧  ጁቬንቱሶች የቦሩሲያ ዶርትመንዱን እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተሰላፊ ጃዶን ሳንቾ ለማዛወር እውነተኛ ፍላጎት አሳድረዋል።  (Source: Calciomercato)

.

➧  የPSG'ው ብራዚላዊ ተመላላሽ ተከላካይ እግርኳስ በቃኝ ብሎ ከማቆሙ በፊት በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጫወት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።
(Source: Daily Telegraph)

.

➧  የማንቸስተር ዩናይትድ ተጭዋቾች ጆዜ ሞሪንዎ አማካዩን ኒማንያ ማቲች በቀጣዩ ጨዋታ ላይ ተጠባባቂ እንዲያደርጉት ይፈልጋሉ።  (Times)

.

➧  ጆዜ ሞሪንዎ ኒማንያ ማቲች አቋሙ መውረዱ በግልፅ እየታየ ባለበት ሁኔታ ላይ ቋሚ ተሰላፊ ማድረጋቸው በተጭዋቾቹ መሃከል ጥያቄ አስነስቷል። አንዳንድ የቡድኑ ተጭዋቾች እና ስታፎች ተጭዋቹ የቱንም ያህል አቋሙ ቢወርድ የማይነካ እንደሆነ አምነዋል።   (times)

.

➧  ሳንቲያጎ ሶላሪ እስከዚህ የውድድር አመት መጨረሻ ድረስ የክለቡ ቋሚ አሰልጣኝ በመሆን ከጊዜያዊ አሰልጣኝነት በቋሚነት ተሹመዋል።  (Source: AS)

.

➧  ማንቸስተር ዩናይትዶች የአንቶኒዮ ቫሌንሺያን ኮንትራት ለተጨማሪ አንድ አመት ለማራዘም ንግግር በማድረግ ላይ ናቸው።   (guardian)

.

➧  የአርሰናሉ ግብ ጠባቂ በርናንዶ ሌኖ እንዳለው ከሆነ ቢድኑ ዎልቭስን ከመግጠማቸው ከጥቂት ሰአታት በፊት በቡድኑ ቅድመ ዝግጅት ስብስብ ወቅት በከባድ ጉዳት ቀዶ ጥገና ያደረገውን አጥቂ ዳኒ ዌልቤክን በpre-match ቡድኑ ውስጥ እንዲካተት በማድረግ ፊት ለፊት አግኝተው እንደጎበኙት አሳውቋል።    (Standard)

.

➧  ቪክቶር ሊንደሎፍ የ2018 የአመቱ የሲውዲን ምርጥ ተጭዋች በሚል የSwedish Golden Ball ሽልማት አሸነፊ መሆን ችሏል።

.

➧  ማንቸስተር ዩናይትዶች የሁለቱን ስፔናዊ አማካዮች ዩሃን ማታ እና አንደር ሄሬራን ኮንትራት ለማራዘም ከተጭዋቾቹ ጋር ድርድር ማድረግ ጀምረዋል።  (men)

.

➧  ማንቸስተር ሲቲዎች የደቡብ አፍሪካውን ከ17 አመት በታች አምበል ግብ ጠባቂ Constandino ወይም በቅፅል ስሙ ‘Costi’ Christodoulou, ለሁለት ሳምንት የሙከራ ጊዜ ሰጥተው ራሱን እንዲያሳይ ጋብዘውታል።    (Times Live)

.

➧  አሌክሳንደር ላካዜቲ ከአርሰናል ክለብ ዶክተሮች ጋር ጥልቅ ምክክር እና ቼክ አፕ ካደረገ በኃላ ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ደርሶት የነበረውን ጥሪ ሳይቀበለው ቀርቷል።   (Mail)

.

➧  ናቢ ኪየታ በሊቨርፑሉ አለቃ የርገን ክሎፕ ስር በመሰልጠኑ 'እድለኛ' እንደሆነ ተናግሯል። ተጭዋቹ አክሎም የእንግሊዘኛ ችሎታውን ለማሻሻል ጠንክሮ ቋንቋውን እያጠናው መሆኑን ገልፆአል።

.

➧  የ2018 የNorthwest Football Awards, በሚል በተዘጋጀው የሽልማት ስነስረአት ላይ የሊቨርፑል ክለብ ተጭዋቾች እና ክለቡ በአምስት ዘርፎች ሽልማት ማግኘታቸው ተሰምቷል። በመድረኩ ላይ የእውቅና ልዩ ሽልማታቸው ያገኙት ግለሰቦች ወይም ቡድኖች በእግርኳሱ ዘርፍ ሜዳ ላይም ሆነ ከሜዳ ውጪ ባለፈው አመት ሲዝን ላይ በሰሩአቸው ውጤታማ ተግባራት የተመረጡ ናቸው። (liverpoolfc)

.

➧  ሽልማት ከወሰዱባቸው ዘርፎች መሃከል ሞሃመድ ሳላህ የPlayer of the Year, ሽልማትን ሲወስድ ተከላካዩ Trent Alexander-Arnold ደግሞ በተስፈኞች ጎራ የhome Rising Star of the Year, በሚል ተሸልሟል። ከሊቨርፑል ሴቶች ቡድን ደግሞ and Niamh መጪ ተስፈኛዋ ሴት ተጭዋች Women’s Rising Star of the Year በሚል ዘርፎች አሸናፊ መሆን ችለዋል።

.

➧  የአርሰናል አካዳሚ ውጤት የተባለውና መጪው የአርሰናል ብሩህ ተስፋ የሆነው በውሰት ለጀርመኑ ቡንደስሊጋ ክለብ የሚጫወተው ሪስ ኔልሰን የቡንደስሊጋው የወሩ ምርጥ ወጣት ተጭዋች ‘Rookie of the Month’ በሚል ተሸልሟል።

.

➧  የጀርመን ብሄራዊ ቡድን ተጭዋቾች እንደሁል ግዜው እንደሚያደርጉት በሌፕዚክ ትምህርት ቤቶች በመሄድ ከተማሪዎቹ ጋር ጥያቄ እና መልስ ያካሂዳሉ። የመጀመሪያው ጥያቄ የተጠየቀው ደግሞ ሎሪ ሳኔ ሲሆን ጠያቂው የአምስተኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ታዳጊ ነው ...

"ሳኔ ሜሱት ኦዚል ካሁን በኃላ ለጀርመን ብሄራዊ ቡድን አይጫወትም። በዚህ ዙሪያ አንተስ ምን ትላለህ?" ሲል ቢጠይቀውም ሳኔ በመሳቅ ሳይመልስለት በዛው አልፎታል።   (Plettigoal)

.

➧  ቼልሲዎች የባርሴሎናውን አማካይ ተጫዋች ዳኒ ሱዋሬዝ በጥርየዝውውር መስኮት ላይ ለማዛወር ፍላጎት አሳድረዋል። ተጭዋቹ በካታላኑ ክለብ በቂ የመሰለፍ እድል እያገኘ ባለመሆኑ ክለቡን ሊለቅ ይችላል።   (90min)

.

➧  ቤንጃሚን ሜንዲ በህመም ምክንያት እራሱን ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጥሪ ካገለለ በኃላ በInstagram አካውንቱ የለጠፈው ..

"በተቻለ ፍጥነት እመለሳለሁ! I’ll be
back asap"

.

➧  ኤደርስን ስለ ማንቸስተር ደርቢ: "ከዩናይትዶች በእጥፍ የተሻልን ነበርን። እንደውም በደንብ ወደፊት ገፍተን መጫወት ብንችል ኖሮ የጎሉ መጠን ከዚህም በላይ በሰፋ ነበር"

 .

➧  የቀድሞው የዌስትሃም፣ ቼልሲ እና እንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አማካይ ጆ ኮል ከእግርኳስ መገለሉን በይፋ አስታወቀ።   (Source:  SkySports)

.

➧  ማንቸስተር ዩናይትዶች የተመላላሽ ተከላካዩን የአሽሊ ያንግን ኮንትራት ለአንድ ተጨማሪ አመት ለማደስ ንግግር እያደረጉ ይገኛል።  (Source: SkySports)

.

➧  ጆዜ ሞሪንዎ ቡድኑን በዚህ የውድድር አመት ላይ በቶፕ 4 ውስጥ ደረጃ ይዞ እንዲጨርስ የማያደርጉት ከሆነ ክለቡ እንደሚያሰናብታቸው ተሰምቷቸዋል። ክለቡ የቶተንሃሙን ሞሪሲዮ ፖቸቲንዎ የፖርቹጋላዊው ምትክ ለማድረግ አቅዷል።  (Source: Sun Sport)

No comments:

Post a Comment