ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Monday 22 October 2018

ክርስቲያኖ ሮናልዶ - የጁቬንቱሱ ኮከብ ከመድፈር ውንጀላ ክሱ ጥላ ጋር ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ለመመለስ ተሰናድቷል



ክርስቲያኖ ሮናልዶ - የጁቬንቱሱ ኮከብ ከመድፈር ውንጀላ ክሱ ጥላ ጋር ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ለመመለስ ተሰናድቷል

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ነገ ለሚደረገው ተጠባቂ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ኦልትራፎርድ አቅንቷል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከሁለት ቀናት በፊት በአምስቱም የአውሮፓ ትልልቅ ሊጎች ላይ 400 ጎሎችን በማስቆጠር ሪከርዱን የጨበጠው ፓርቹጋላዊ ኮከብ አሁንም የትኩረት ማዕከል ሆኑአል።

የ33 አመቱ ሮናልዶ ከነዛ ጎሎች መሃከል 84ቱን ያስቆጠራቸው በፕሪሚየር ሊጉ ሲሆን የብቃት መውረድ ምልክት እስካሁን አልታየበትም።

ጁቮንቱሶች ከጄኖዋ ጋር ያለፈው ቅዳሜ 1ለ1 በመውጣታቸው በዚህ የውድድር አመት ለመጀመሪያ ግዜ በሴሪአው ነጥብ ጥለዋል።

ሆኖም የቡድናቸው አውራ ግን ወደ ኦልትራፎርድ ሲመለስ በጎል ማስቆጠር አስደናቂ ብቃቱ ቀጥሎ ጥሩ አቋም ላይ በማይገኙት ዩናይትዶች ላይም ጎል ለማስቆጠር ተስፋ አድርጓል።


ፖርቹጋላዊው ኮከብ ሮናልዶ በቀድሞዋ አሜሪካዊት ሞዴሊስት ካትሪን ማዮርጋ የመድፈር ክስ ቀርቦበት እራሱን ከውንጀላው ነፃ ማድረግ ሳይችል ውዝግቡ አሁንም ቀጥሏል።

አሜሪካዊቷ የ34 አመት እንስት እ.ኤ.አ በ2009 ጉዳዩን እንድትደብቅ የ£287,000 ከመፈፀሙ በፊት ላስ ቬጋስ በሚገኝ ሆቴል የወሲብ ጥቃት አድርሶብኛል ስትል ከሳዋለች። ሆኖም ፓርቹጋላዊው ኮከብ ወዲያውኑ ክሱ ሃሰት መሆኑን ተናግሯል።

በትውልድ መንደሩ ፉንቻል የCR7 Museumን በሃላፊነት እየተቆጣጠረ ያለው የአምስት ግዜ የBallon d'Or አሸናፊው ወንድም የሆነው ሁጎ አሺየሮ የቀድሞው የሪያል ማድሪዱን ኮከብ ክስ ተከላክሎለታል።

የ43 አመቱ ለTimes ጋዜጣ እንዳለው : "የኔ ወንድም በማይዴይራ እንደ ጀግና ነው ሚቆጠረው።

"ለዚች ደሴት ብዙ በጎ ነገሮችን ስላደረገ በማህበረሰቡ ልብ ልዩ ቦታ ተሰጥቶታል። በየአመቱ ሙዚየሙን ለመጎብኘት ከመላው አለም ግማሽ ሚሊዮን ጎብኚዎች ወዲህ ይመጣሉ።

ወንድሜ ወደዚህ ብዙ ግዜ የሚመጣው ለአዲስ አመት ነው። ምክንያቱም ዋዜማው ላይ የእናታችን የልደት ቀን ነው። ምንም እንኳን በዚህ አመት ወደ ዱባይ ሊሄድ ቢችልም የደሴቲቷ ሰዎች ግን በናፍቆት ይጠብቁታል። ሁሉም በደንብ ስለሚያውቁት ስለሱ ውንጀላ ክስ ይከላከሉለታል።

"የአካባቢው ዜና አውታሮች ስለርሱ መልካም ነገሮችን ነው ሚዘግቡት። ህዝቡም ከጎኑ ይቆማል እርሱ የማይዴይራ ልዩ ምልክት ነው"  ሲል አስተያየቱን አጠቃሏል።

No comments:

Post a Comment