ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Sunday 28 October 2018

ዕለተ እሁድ ምሽት ላይ የወጡ በርካታ አጫጭር የዝውውር ዜናዎች፣ የእግር ኳስ ወሬዎች እና አስተያየቶች



♦  PSGዎች የሪያል ማድሪዱን አማካይ ቶኒ ክሮስ ለማዛወር የቻሉትን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ሆነዋል። የክለቡ ባለቤት ጀርመናዊው አማካይን ወደ ፓሪስ ለመውሰድ አስፈላጊውን የዝውውር ሂሳብ ለማውጣት ፍቃደኝነታቸውን አሳይተዋል።
(Source: Mundo Deportivo)

.

♦  ቶሬራ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ስለመዛወሩ:

“በጣም ደስተኛ ነኝ። ትልቅ ፈተና ነው እዚህ አዲስ ፈተናም ነው ለኔ። እኔ እንደዚህ አይነት ፈተናዎችን መጋፈጥ የምወድ ሰው ነኝ። በመንገዴ ሁሉ ተፋልሜ ማሸነፍና ማለፍን የምመርጥ ሰው ነኝ። አባቴ እንዳስተማረኝ መንገዴን ያለ ፍልሚያ ማለፍ አልፈልግም"

.

♦  ቶሬራ ስለ እንግሊዝ እና ጣሊያን ሊጎች ስላሉት ልዩነቶች ተጠይቆ ሲመልስ:

"በዚህ አጭር ግዜዬ የተረዳሁት ነገር ቢኖር በእንግሊዝ እግር ኳሱ እጅግ በጣም ጥብቅ ነው፤ ጉልበት ፍትጊያ የሚበዛበት ሊግ ነው። የጎል ማግባት እድል ለመፍጠር የሦስት አሊያም አራት ኳስ ንክኪ ማድረግ በቂህ ነው። ይሄንን በሴሪአው አታዩትም። እግርኳሱ እንደዚህ ክፍት አይደለም ስፔስ አታገኝም በታክቲኩ የታጠረ ነው።"

.

♦  ጆዜ ሞሪንዎ ዛሬ ከኤቨርተን ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ማርሻል፣ ራሽፎርድ፣ እና ሳንቼዝን ቋሚ ተሰላፊ ለማድረግ ወስነዋል። ሮሚዮ ሉካኩን ለመጀመሪያ ግዜ ተጠባባቂ ወንበር ላይ ሊያስቀምጡትም ተሰናድተዋል።  [MEN እና mail]

.

♦  ፖል ፖግባ ከጁቬንቱሱ ጨዋታ በኃላ: "አስተያየት መስጠት መናገር አልችልም። እንድናገር አልተፈቀደልኝም። ብናገር ደስ ይለኝ ነበር ሆኖም አስተያየት እንዳልሰጥ ተከልክያለሁ"
[Telegraph]

.

♦  ሊቨርፑሎች ካርዲፍ ሲቲን ሲያሸንፉ ያሳዩትን የቡድን ረሃብ እና የማሸነፍ ፍላጎት እስከ ሲዝኑ መጨረሻ ድረስ ይዘው መቀጠል እንዳለባቸው ቴርዳን ሻቂሪ አሳስቧል።

“በጣም ጥሩ የሆነ ቡድን አለን። ከዚህ ቡድን ጋር ስኬትን ማጣጣም እንፈልጋለን። እንደዚህ የምንጫወት ከሆነ ስኬታማ እንሆናለን።"
(liverpoolfc)

.

♦  የርገን ክሎፕ: “አምስት ክለቦች በሊጉ እጅግ በጣም የተቀራረበ ከፍተኛ ነጥብ መያዛቸው ያስገርማል። ፉክክሩ ሊጉን በጣም ያደምቀዋል። ለተመልካቹ ለደጋፊዎቹ ለሁሉም ደስ የሚል ስሜት ይሰጣል። ለኛ ዛሬ እንደዚህ መጫወታችን ለቀጣይ ጨዋታዎች ይጠቅመናል። ቢያንስ አሁን ከድካም የምናገግምበት በቂ ጊዜ አለን"  (mirror)

.

♦  አልፎንሶ ዴቪድስ ስለ ባየር ሙኒክ ዝውውሩ ተጠይቆ ወደ ጀርመኑ ክለብ መቼ እንደሚቀላቀል እና ልምምድ እንደሚጀምር ምንም ነገር እንደማያውቅ ተናግሯል። ሆኖም ለክለቡ ይፋዊ ፊርማውን ካኖረ በኃላ ከመሃል ተከላካዩ ማትስ ሃምለስ ጋር በየጊዜው እንደሚወያይ ተናግሯል።  (iMiaSanMia)

.

♦  ጁቬንቱሶች የማንቸስተር ሲቲውን ፊል ፎደን ለማዛወር ከክለቡ ጋር 'ትልቅ ጨዋታ' ለመጫወት ተዘጋጅተዋል። በፎደን እና በክለቡ ሲቲ መሃከል በቅርቡ ኮንትራቱ ዙሪያ ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ የያዙ ሲሆን ጁሼንቱሶች ጉዳዩን በቅርበት ሆነው በመከታተል ትንሽ ያለመስማማት ክፍተት ካገኙ ጣልቃ ለመግባት ዝግጁ ሆነዋል።  [Mirror]

.

♦ ምንም እንኳን ገና በኢትሃድ ለአራት ተጨማሪ አመታቶች የሚያቆየው ውል ኮንትራቱ ላይ ቢኖረውም በርናንዶ ሲልቫ በማንቸስተር ሲቲ አዲስ ኮንትራት የሚቀርብለት ቀጣዩ ተጭዋች ሆኑአል። ሲቲዎች በርናንዶን የዴቪድ ሲልቫ ትክክለኛ ምትክ አድርገው የሚያዩት ሲሆን እያሳየ ላለው ድንቅ ብቃት አዲስ ኮንትራት እንደ ማበረታቻ ሊሰጡት ይፈልጋሉ።
[Mirror / The Sun]

.

ማንቸስተር ሲቲዎች የአያክሱን አማካይ ፍራንክ ዲ ጆንግን በጥር የዝውውር መስኮት ላይ የክለባቸውን የዝውውር ሪከርድ በመስበር ሊያስፈርሙት ይችላሉ፤ ከዛም እስከ ሲዝኑ መጨረሻ ድረስ ለአያክሶች መልሰው በውሰት በመስጠት ቅድመ ስምምነት ላይ በመድረስ ተጭዋቹን በክረምት በይፋ ወደ ኢትሃድ ሊወስዱት አቅደዋል። ምንም እንኳን ቶተንሃም፣ ማን.ዩናይትድ፣ ባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድን የመሳሰሉ በርካታ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች
ተችዋቹን ማዛወር ቢፈልጉም ማንቸስተር ሲቲዎች ግን በአውሮፓ መጪዎቹ ከዋክብቶች አንዱ ነው የተባለለትን ሆላንዳዊ ባለተሰጥዎ አማካይ የማዛወር የተሻለ እድል አላቸው።  [Daily Star Sunday]

.

የቶተንሃሙ አማካይ ዴል አሊ በክለቡ ለተጨማሪ አመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ለመፈራረም ተቃርቧል።   (Source: SkySports)

.

እንደ በርካቶች ዘገባ ከሆነ አንቶኒዮ ኮንቴ አዲሱን የሪያል ማድሪድ ስራ ለመረከብ ዝግጁ ሆነው በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ሎፕቲግ በዛሬው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ የሚሸነፉ ከሆነ ከፍሎረንቲኖ ፔሬዝ የስንብት ደብዳቤ ይደርሳቸዋል።   (Sky)

.

ማውሪሲዮ ሳሪ የ18 አመቱን ባለተሰጥዎ ታዳጊ ተጭዋች ሳንድሮ ቶናሊን ለማዛወር ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። ሆኖም በዝውውሩ ላይ ከጁቬንቱሶች ጋር ከፍተኛ ፉክክር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።  (90min)

.

ምንም እንኳን በቅርብ የወጡ ሪፖርቶች እንዳመላከቱት ከሆነ የለንደኑ ቼልሲ ክለብ ለአንድ አውሮፓዊ ቢሊየነር ባለሃብት ሊሸጥ ይችላል የሚሉ ዘገቦች ቢሰሙም የክለቡ ባለቤት ሩሲያዊው ባለሃብት ሮማን አቭራሞቪች ግን ክለቡን የመሸጥ ምንም ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለፅ ሪፖርቶቹን አጣጥለዋል።  (90min)

.

በጁላይ ወር ላይ የእግርኳስ ልምምድ ለማድረግ በሚል ከከተማ ውጪ ወጥተው ሳለ በወቅቱ ልምምድ ላይ ሳሉ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ ለመጠለል ሲሉ ዋሻ ውስጥ ገብተው የመሬት መንሸራተት ተከስቶ በዋሻው ውስጥ ተቀብረው በሞት እና በህይወት መሃከል ሆነው በመጨረሻ መትረፍ የቻሉት የታኢ ታዳጊዎች እና አሰልጣኛቸው በኦልትራፎርድ ተጋብዘው ከጆዜ ሞሪንዎ እንዲሁም ከተጭዋቾቹ ጋር አስደሳች ግዜያትን ያሳለፉ ሲሆን ዛሬ ቡድኑ ከኤቨርተን ጋር በሚያደርገው የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታ ላይ በኦልትራፎርድ በልዩ ተጋባዦች ቦታ  ስፍራ ሆነው ጨዋታውን እንደሚመለከቱ ተገልፆአል።
[BBC]

.

የሌስተር ሲቲው ክለብ ባለቤት የግል ሄሊኮፕተር ከኪንግስ ፓወር ስቴዲየም ውጪ ተከስክሳለች።
እንደ Sky ምንጮች ከሆነ የክለቡ ባለቤት በፕሌኑ ላይ ተሳፍረው ከነበሩ አምስት ግለሰቦች አንዱ መሆናቸው ታውቋል።  (SkySport)

.

ሂሊኮፕተሩአ ከስቴዲየሙ ውጪ መኪና ማቆሚያ ስፍራ ላይ ለመብረር ተነስታ ጥቂት ከፍታዎችን ከተነሳች በኃላ ሲሆን የተከሰከሰችው እስካሁን ስለደረሰው ጉዳትም ሆነ ሞት ምንም የተባለ ነገር የለም። የክለቡ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሺማይክል በስቴዲየሙ ዙሪያ እስከ ጠዋቱ 1 ሰአት ድረስ በእንባ እና በሃዘን ስሜት ሆኖ እዛው እንደቆየ ተነግሯል።   (dailymail)

.

የሌስተር ሲቲ ክለብ የቡድኑ ተጭዋቾች ዛሬ ሊያደርጉ የነበሩትን የልምምድ ፕሮግራም በመሰረዝ ተጫዋቾቹ ቤታቸው እንዲቆዩ አድርገዋል። ክለቡ የፊታችን ማክሰኞ በካራቦን ካፕ ከሳውዛምፕተን ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ቀንም እንዲራዘምላቸው ጠይቀዋል።  (dailymail)

No comments:

Post a Comment