ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Friday 9 November 2018

አርብ ምሽት የወጡ በርካታ የዝውውር እና ሌሎችም ዜናዎች

ጁቬንቱሶች አንቶኒ ማርሻልን ከማንቸስተር ዩናይትድ ለማዛወር የነበራቸው እቅድ ላይ ተስፋ ቆርጠዋል። በዚህ ምክንያት ትኩረታቸውን በቦሩሲያ ዶርትመንዱ አጥቂ ጃዶ ሳንቾ አዙረዋል።   (Source: Daily Express)

.

የበርንማውዙ አጥቂ ካሉም ዊልሰን በ£35m የዝውውር ዋጋ የቼልሲ የዝውውር ኢላማ ሆኑአል። የ26 አመቱ አጥቂ ትላንትና ለመጀመሪያ ግዜ ወደ እንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ተጠርቷል።   (Source: Sun Sport)

.

ባየር ሙኒክ፣ ቦሩሲያ ዶርትመንድ እና አርሰናሎች የሊሉን የክንፍ መስመር የ23 አመቱን ተጫዋች ኒኮላስ ፔፔ ለማዛወር የ €50 ሚሊዮን ዩሮ ሂሳብ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። 8 አስቆጠረ 7 ለጎል አቀበለ in 13 ተጫወተ። (telefoot_TF1)

.

አንቶኔ ማርሻል ወደ ፈረንሳይ ብሄራቡ ቡድን በድጋሚ ተጠርቷል።   (l’equipe)

.

አርሰናሎች የጁቬንቱሱን መሃል ተከላካይ መሃዲ ቤናሺያን ለማዛወር በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ጥያቄአቸው ያቀርባሉ። መድፈኞቹ እንደሚያምኑት ከሆነ የጁሼንቱሱ መሃል ተከላካይ በቱሪን ህይወቱ ደስተኛ አይደለም።   (Source: Daily Star)

.

ኦዚል ስለ ኡናይ ኢምሬ: “አሁን በጥሩ መንገድ ላይ ነን። በዚሁ ሁኔታ መቀጠል እንፈልጋለን። በጣም ጥሩ አሰልጣኝ ነው። ተጭዋቾችን መረዳት ይፈልጋል ሁሌም ከጎናችን ይሆናል። ክለቡን በደንብ ተረድቶታል። ሜዳ ላይ ሁላችንም ያለንን ልናሳየው የምንጓጓለት አይነት አሰልጣኝ ነው"

.

ሙስታፊ ስለ ቶሬራ: “ለስኬቱ ደስተኛ ነኝ። የቀድሞ ክለቤ በሆነው ሳምፕዶሪያ ተጫውቷል። እንደዚህ በቀላሉ የሚለመድ ሊግ አይደለም። በእንግሊዝ እና በጣሊያን ያለው ፈፅሞ ይለያል። እኔ በደንብ እረዳለሁ ምክንያቱም በተለያዩ ሃገራት ሊጎች ተጫውቼ አሳልፌአለው። እንደርሱ በፍጥነት መላመድ ከባድ ቢሆንም እርሱ ግን በሚገባ ተላምዶ ጥሩ ነገር እያሳየን ነው።"

.

ሳሙኤል ኤቶ ተስፋ በቆረጠ ሰአት ለሊቨርፑሉ ኮከብ ሙሃመድ ሳላህ የእግርኳስ ህይወቱን የቀየረለትን ምክር ሰትቶት እንደነበር ተናግሯል።

"ነገሮች ባሰበው መልኩ ባለመሄዳቸው ተስፋ ቆርጦ ነበር እንዲታገስ መከርኩት። 'አንተ በጣም ጥሩ ተጭዋች ነህ ወደፊት ታላቅ ተጭዋችም ትሆናለህ' ስል ምክሬን ለግሼዋለሁ"

"ሁሉም ነገር የሚወሰነው በራሱ በሳላህ ነው። የማይታመኑ ክህሎቶች አሉት። እናም አሁን በትልቅ ደረጃ እየተጫወተ ይገኛል። የባለን ደ ኦር እጩም መሆን ችሏል"

.

ጆርዳን ሄንደርሰን፣ ትረንት አሌክሳንደር አርኖልድ እና ጆ ጎሜዝ በእንግሊዝ በሄራዊ ቡድን አለቃ ጋሬዝ ሳውዝጌት ቡድኑን እንዲቀላቀሉት ጥሪ ደርሷቸዋል።

.

ማትስ ሁምለስ: "ይሄኛው የቦሩሲያ ዶርትመንድ ቡድን በየርገን ክሎፕ ዘመን የነበረውን ድንቅ ቡድን ያስታውሰኛል"  (Bild)

.

ፑማ ተጨማሪ የማንቸስተር ሲቲ ተጭዋቾችን ስፖንሰር ለማድረግ እየጣረ ነው። ሎሪ ሳኔ፣ ቪሰንት ኮምፓኒ እና ራሂም ስተርሊንግ በራዳራቸው ውስጥ ገብተዋል። ከሲቲ ጋር ፑማዎች አመታዊ የ£50m ክፍያ ስፖንሰርሺፕ ተፈራርመዋል። ዴቪድ ሲልቫና ሰርጂዎ አጉዌሮም ቀደም ብለው ለፑማ ፊርማቸውን አኑረዋል።   (Daily Mail)

.

ፍሬድ ለFourFourTwo: "ሲቲዎች ጥያቄ አቅርበውልኝ እንደነበር ሚነገረው እውነት ነው። እናዛውርህ ብለውኝ ነበር። እንደውም በብሄራዊ ቡድን አጋሬ በኩል እንድቀላቀላቸው ሊያሳምኑኝ ሞክረው ነበር። ሆኖም በመጨረሻ ዝውውሩ ሊሳካ አልቻለም"

.

ዌስትሃም ዩናይትዶች የ31 አመቱን የቀድሞ የማንቸስተር ሲቲ አማካይ ሳሚር ናስሪ ለማዛወር እያጤኑበት ነው። የቀድሞው የፈረንሳይ ኮከብ በእፅ መውሰድ ክስ ከተጣለበት የ18 ወራት የጨዋታ ቅጣት በቅርብ ወደ ሜዳ ይመለሳል።  (Mirror)

.

ማንቸስተር ሲቲዎች ታዳጊውን ፈርናንዶ ኦቬላርን ለማዛወር እየተከታተሉት ይገኛሉ። ኦቨራባለፈው ሳምንት በፓራጓዩ ሱፐርክላሲኮ ጩዋታ ላይ ጎል ማስቆጠር ችሏል - ምንም እንኳን ገና 14 አመቱ ቢሆንም።  (Mirror)

.

ማንቸተር ዩናይትዶች የሳምፕዶሪያውን የ22 አመት ዴንማርካዊ ተከላካይ ኮአኪም አንዴርሰንን የማዛወር ፍላጎት አላቸው።   (Source: La Republica)

.

ኒኮላስ ፔፔ ሊልን ለመልቀቅ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ። ይሄንን ተከትሎ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ወደ አርሰናል ሊዛወር ይችላል በሚል በስፋት እየተወራ ይገኛል።   (Source: Sun Sport)

.

ጃቪ ጋርሺያ የዋትፎርድ ዋና አለቃ በመሆን አዲስ የቀረበላቸውን የሦስት አመት ኮንትራት ለመፈራረም ተስማምተዋል።   (Source: SkySports)

.

ኤቨርተኖች እድሜአቸው ከ10-18 የሆኑ ታዳጊ ተጭዋቾችን ለሁለት አመታት እንዳያዛውሩ እገዳ ተጭሎባቸዋል። ይሄ የሆነው ታዳጊዎችን ገና የትምህርት ገበታቸው በማማለል ለማዛወር ሲያደርጉ የነበረው ጥረት ተደርሶበት ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ ነው።   (Source: SkySports)

.

ቼልሲዎች እና ባየር ሙኒኮች የሊዮኑን አማካይ አጥቂ ናቢ ፊከር ለማዛወር በድጋሚ ተፋጠዋል። ተጭዋቹ በቀጣዩ ክረምት ላይ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ በግልፅ ነግሮአቸዋል።   (Source: L'Equipe)

.

የPSVው ኮከብ አጥቂ ሄርቪንግ ሎዛኖ አሁን ያለበትን የሆላንዱን ክለብ የሚለቅ ከሆነ ከማንቸስተር ዩናይትድ አሊያም ባርሴሎና አንዳቸውን ብቻ እንደሚቀላቀል ተናግሯል።  (Source: Sun Sport)

No comments:

Post a Comment