ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Thursday 1 November 2018

አርሰናል እና ማን ዩናይትድ በድጋሚ ተጭዋቾችን ሊለዋወጡ፤ ስተርሊንግ ከውሳኔ ላይ ደርሷል



SWITCHEROO የአርሰናሉ ኮከብ አሮን ራምሴይ እና የማንቸስተር ዩናይትዱ ኮከብ ጁሃን ማታ ክለቦቹ ሊቀያየሩ ነው ሲሉ ትልልቅ አቋማሪ ድርጅቶች ጠቆሙ

ሁለቱም ተጭዋቾች በክረምቱ ከኮንትራት ነፃ የሚሆኑ ሲሆን ከባለፈው አመት ጥር ወር እንዳደረጉት የተጭዋቾች ቅይይር አሁንም ለማድረግ ወጥነዋል

የአርሰናሉ ኮከብ አሮን ራምሴይ የጥር የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ በማምራት በተቃራኒው ዩሃን ማታ ወደ ኤምሬትስ ሊዛወሩ ነው ሲሉ የእንግሊዝ አቋማሪ ድርጅቶች ጠቁመዋል።

ሁለቱም የአማካይ ስፍራ ተጭዋቾች ከኮንትራት በክረምቱ ነፃ መሆናቸውን በመረዳት ያለምንም ክፍያ ከሚለቋቸው ይልቅ ቢቀያየሩአቸው እንደሚጠቀሙ ይረዳሉ።

ዩሃን ማታ በጆዜ ሞሪንዎው የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድን ውስጥ በቋሚነት የመሰለፍ እድል የተነፈገው ሲሆን አርሰናሎች በበኩላቸው ባለፈው ጥር ወር ላይ አሌክሲስ ሳንቼዝን በሄነሪክ ሚኪተሪያን በመለወጥ ለልውውጥ ዝውውር አዲስ አለመሆናቸው ይታወቃል።

እንደ አቋማሪዎቹ ከሆነ ዩሃን ማታ ወደ አርሰናል የመዛወር እድሉ ከ8/1 ወደ 7/4 በአንድ ምሽት የሠፋ እድል እንዳለው ጠቁመዋል።

ስፔናዊው ኢንተርናሽናል የአርሰናሉን አለቃ ኡናይ ኤምሬ ትክክለኛው አሰልጣኜ(በ 2008-2011 የውድድር አመት በቫሌንሺያ አብረው ሰርተዋል) ሲል በማሞካሸት ወደ ኤምሬትስ ሊዛወር ይችላል የሚል ጭምጭምታውን እንዲጠናከር አድርጓል

በሌላ በኩል አቋማሪዎቹ የአሮን ራምሴይን ወደ ኦልትራፎርድ የመዛወር እድል እንዳለው 4/1 በማድረግ አቃርበውልታ።

በሌላ ዜና ...

RAHEEM STERLING በማንቸስተር ሲቲ የሚያቆየውን አዲስ የረጅም አመት ኮንትራት ለመፈራረም ከስምምነት ላይ ደረሰ።

የ23 አመቱ እንግሊዛዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች በ2020 ላይ በሚጠናቀቀው አዲስ ውሉ ላይ ኮንትራቱን ለማደስ በማንገራገሩ በክለቡ ሰዎች ይለቅ ይሆን በሚል ስጋት ውስጥ እንዲሆኑ አድርጎ ነበር። ሆኖም እንደ ሪፖርቶች ዘገባ ከሆነ አዲስ ስምምነት ለመፈራረም በቃል ደረጃ ከስምምነት ላይ ደርሷል።

የ23 አመቱ ክንፍ ወደ ሪያል ማድሪድ ይዛወራል የሚለውን የቅርብ የዝውውር ጭምጭምታ ወደጎን በመተው በኢትሃዱ ክለብ እስከ 2023 ድረስ የሚያቆየውን ውል ለመፈራረም ተስማምቷል ሲሉ የSky Sports ዘጋቢዎች ተናግረዋል።

(ምንጭ ፦ TheSun)


No comments:

Post a Comment