ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Sunday 28 October 2018

በሳምንቱ መጨረሻ የወጡ ያልሰሟቸው ልዩ የእግር ኳሱ ዜናዎች - News You Missed TODAY



የአውሮፓ ትልልቅ ክለቦች በድብቅ ውይይት አድርገዋል ሲል ዘሰን ጋዜጣ ደርሼበታለሁ ሲል ዘግቦታል። የእግር ኳሱ ግዙፍ ክለቦች ተጭዋቾች እየጠየቁ ባለው ውድ የደሞዝ ፓኬጅ አማሮአቸዋል፤ መፍትሄ ሊያበጁለትም ተሰብስበው መክረዋል

ክለቦቹ ባሁን ዘመን ተጭዋቾችን ለማዛወር እና በክለቡ ያላቸውን አዲስ ኮንትራት አድሶ ለማፈራረም እየጠየቁአቸው ያለው እጅግ በጣም የተጋነነ ሳምንታዊ ክፍያ በወደፊት የክለቦቻቸው ቀጣይነት እጣ ፈንታ ላይ ሳይቀር እየተፈታተነባቸው በመሆኑ መፍትሄ ሊያበጁለት ውይይት አድርገዋል።

ክለቦቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተተኮሰ የመጣውን ደሞዝ ጥያቄ በህብረት በመሆን ስለሚያስቆሙበት ሁኔታ የመከሩ ሲሆን በእንቅስቃሴው ንቁ አስተባባሪነት ሚናን እየተወጡ ያሉት የአርሰናል ክለብ ባለስልጣናት የአሮን ራምሴይ ረብጣ ደሞዝ ጥያቄ እንቅስቃሴውን እንዲያፋጥኑት እንዳደረጋቸው ተገልፆአል።

አሮን ራምሴይን ፍላጎት አናሟላም ያሉት አርሰናሎች ራሳቸውን ከድርድሩ አግልለዋል። ራሂም ስተርሊንግ በበኩሉ ጨምሩልኝ ያለውን ሳምንታዊ ተጨማሪ የ£100,000 ደሞዝ ክለቡ እንደማይሰጠው ነግሮት እስካሁን አልፈረመም።

________________________________________

የሊዮኔል ሜሲ ልጅ ቲያጎ በባርሴሎና ጨዋታ ላይ ለአባቱ ስሎ ያሳየው ስዕል ምን እንደሆነ ታወቀ..

በእለቱ በቻምፒየንስ ሊጉ ባርሴሎናዎች ኢንተር ሚላንን 2ለ0 ሲያሸንፉ አርጀንቲናዊው ኮከብ በጉዳት ምክንያት ጨዋታውን ከልጁ ቲያጎ ጋር በመሆን በስቴዲየሙ ተቀምጦ ለመመልከት ተገዶ ነበር።

በእለቱ ቲያጎ የተለያዩ ስዕሎችን በA4 ወረቀት ላይ በመሳል አባቱን በስቴዲየሙ እንዳይደብረው ሲያዝናናው ታይቷል።

ስሎ ከሰጠው ምስል መሃከል የጁቬንቱስ ክለብ ይፋዊ ሎጎ መሆኑን ከነሱ ጀርባ በመሆን ምስል በማሳት ይፋ ያደረገው የካምፕኑ ተመልካች የለቀቀው ፎቶ አመላክቷል።

________________________________________

የክርስቲያኖ ሮናልዶ ምርጥ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ከሜዳ ውጪም ውጤታማ እያደረገው ሃብቱን እያደለበለት ይገኛል።

የጁቬንቱሱ ኮከብ በስሙ የተመዘገበ ከ400 ሚሊዮን ዩሮ በላይ የባንክ የገንዘብ መጠን ያለው ሚሊየነር መሆኑ ይፋ ሆኑአል።

ከጥሬ ገንዘቡ በመተጨማሪ ክርስቲንኖ ሮናልዶ አሁን ያለውን የገበያ ሁኔታ ላይ በስፋት በመግባት የተለያዩ ትላልቅ ድርጅቶች ባለቤት መሆኑ ይታወቃል።

ተጭዋቹ ከማን.ዩናይትድ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ የ£750,000 ዋጋ የሚያወጣ ከዳይመንድ የተሰራ የእጅ ሰአት አድርጎ መታየቱ ሊያስደምምዎት ይችላል።

ሆኖም ተጭዋቹ CR7 የተባሉ የሆቴሎች ባለቤት፣ በማዴይራ በሚሊየኖች የሚጎበኝ ሙዚየም ባለቤት ነው።

ከዚህ በተጨማሪም በድምሩ የአለም ሪከርድ የሆነ የማህበራዊ ተከታዮች (ከ277 million በላይ), ያለው ሲሆን በስሙ የሚመረቱ የፋሽን ልብሶች፣ ነጭ የውስጥ ሱሬዎች እና ሽቶዎችን የሚያመርቱ ድርጅቶችም ባለቤት እንደሆነ በቅርቡ ስለርሱ የተሰራው ዶክመንተሪ ፊልም ያሳየው ጉዳይ ነው።

________________________________________

የማንችስተር ዩናይትድ ባለቤት የሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች ለሆዜ ሞሪንሆ ማስጠንቀቂያ መላካቸው ተሰማ፡፡

ከ2005 አንስቶ የክለቡን አብላጫውን አክሲዮን በመግዛት ቀያይ ሰይጣኖቹን እያስተዳደሩ የሚገኙት የግሌዘር ቤተሰቦች ፖርቱጋላዊው አለቃ ከሚዲያ እና ከስቴዲየም ስርዓት ጋር በተያያዘ እያደረጉት ያለው ነገር የክለቡን ገጽታ እያበላሸ ነው በሚል ሞሪንሆ ከዚህ ድርጊት እንዲተቃቀቡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ዘ ሰን አስነብቧል፡፡

በተያያዘ ዜና ዩናይትዶች በነፃ ዝውውር የተለቀቀውን የኒውካስል እንግሊዛዊ ኢንተርናሽናል ግብ ጠባቂ ፖል ዎልስተንን ወደ ክለቡ ለማዛወር ስምምነት አድርገዋል።

የ20 አመቱ ግብ ጠባቂ ፖል ዎልስተን በክረምቱ ከኒውካስል ሁለተኛ ቡድን ትርፍ ነህ በሚል የተለቀቀ ሲሆን ዩናይትዶች የአንድ ወር የሙከራ ጊዜ ሰጥተውት ቀድመው አይተውት ነበር።  ለተጨዋቹ የአንድ አመት ኮንትራት በመስጠት የቡድናቸው ከ21 አመት በታች ስብስብን እንዲቀላቀል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ስቴዲየምን ባለሞቆጣር በሚል በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ቅጣት ሊጣልበት መሆኑ ተሰምቷል፡፡

________________________________________

ሞኦሪሲዮ ፖቸቲንዎ ከትላንቱ የክለቡ ልምምድ ፕሮግራም ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

ምንም እንኳን ቡድናቸው ቶተንሃም ከነገ በስቲያ ወሳኝ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ከማንቸስተር ሲቲዎች ጋር የሚያደርግ ቢሆንም አርጀንቲናዊው አሰልጣኝ ክለቡን ፍቃድ በመጠተቅ ከልምምድ ፕሮግራሙ ቀርተው እረፍት አድርገዋል።

በዌምብሌይ ሜዳ ብልሽት ምክንያት የሰኞው ምሽት ጨዋታ ሳቢ ላይሆን ይችላል በሚል በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መነጋገሪያ ሆኖ ሳለ፤ ሞሪሲዮ ፖቼቲንዎ ደግሞ የልምምድ ፕሮግራማቸውን በሚያምኑአቸው ምክትላቸው ሊውትናንት ጂሰስ ፔሬራ እንዲመራ አድገው ሌላ መነጋገሪያ ርዕስ ፈጥረዋል።

1 comment: