ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Thursday 8 November 2018

ሃሙስ ምሽት የወጡ የዝውውር እና ሌሎችም ዜናዎች Latest News Updates



PAUL POGBA MISSED MAN UNITED TEAM FLIGHT AFTER WIN OVER JUVENTUS

ፖል ፖግባ ከትላንት ምሽቱ የማን.ዩናይትድ ቻምፒየንስ ሊግ ጁቬንቱስ ድል በኃላ ወደ ማንቸስተር ከተማ በተመለሰው የተጭዋቾቹ በረራ ፕሌን ውስጥ አልነበረም ተባለ።

ፈረንሳዊው ኮከብ ወደ ማንችስተር የተመለሰው ከተጭዋቾቹ ጋር ሳይሆን ከክለቡ ዋና አስተዳዳሪ እና ከደጋፊዎች ጋር ዋናው ቡድን የያዘው ፕሌን ማንቸስተር ከገባ ከአንድ ሰአት በኃላ ነው።

ይሄ የሆነበት ምክንያት ቡድኑ ታሪካውን ድል በቱሪን ካስመዘገበ በኃላ የአደንዛዥ እፅ መርማሪ ቡድኖች ፖግባ ላይ የሽንት እና መሰል ሳምፕሎችን በመውሰድ ምርመራ ለማድረግ ጠርተውት ከበረራው ስላዘገዩት ነበር ተብሏል።   (ምንጭ፦ Mirror)

ARSENAL SCOUT BRAZILIAN STAR SIX TIMES

አርሰናሎች የጥር የዝውውር መስኮቱ ተከፍቶ ወደ ዝውውሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት የብራዚላዊውን ኮከብ እንቅስቃሴ ለ6ተኛ ግዜ ገምግመዋል ተባለ።

የ18 አመቱ ታዳጊ ተጭዋች ሙሉ ስም Eric dos Santos Rodrigues (በቅፅል ስሙ ራሚሬዝ ይሉታል) የሚባል የአማካይ ስፍራ ተጭዋች ሲሆን ለብራዚሉ ባሂአ የተሰኘ ክለብ በመጫወት ላይ ይገኛል። በአትሌቲኮ ማድሪድም ይፈለጋል።

ገና በለጋ እድሜው በብራዚሉ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ላይ በ9 ጨዋታዎች ላይ መሰለፍ ችሏል። ከደቡብ አሜሪ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ ተጭዋቹ በጥር ላይ ወደ አርሰናል ሊያመራ ይችላል።
ክለቡ ባሂያ መጪው የብራዚል ባለተሰጥዎ ኮከብ እየተባለ የሚወደሰውን ኮከብ ለሃገር ውስጥ ክለቦች አሳልፈው ከመሸጥ ይልቅ ወደ አውሮፓ ትልልቅ ክለቦች ለመሸጥ ምርጫቸውን ማድረጋቸው ራሚሬዝ ቀጣይ ማረፊያው የለንደኑ ክለብ ነው እንዲባል አሰኝቷል።  (ምንጭ፦ The Sun)

PETER CROUCH CAR WAS STOLEN FOR SEX CAUSE

የዝነኛው እንግሊዛዊ አጥቂ ፒተር ክራውች ውድ መኪና በአንድ ሌባ ከተሰረቀች በኃላ - ዘራፊው የኃላውን መቀመጫ ቦታ ስፍራ ላይ ወሲብ እንደፈፀመበት ተጭዋቹ ተናገረ።

የቀድሞው የእንግሊዝ እና የሊቨርፑሉ አጥቂ በታዋቂው የBBC Podcast ሾው ፕሮግራም ላይ አንድ ደጋፊ በስልክ ደውሎ ከጠየቀው በኃላ ነው ጉዳዩን በቀጥታ ይፋ ያደረገው።

አድማጩ ጄይ የሚባል ሲሆን በቀጥታ የሬዲዮ ፕሮግራሙ ላይ ከደወለ በኃላ የተጭዋቹ መኪና ጠፍታ በነበረችበት ወቅት ከኃላ ወንበር መቀመጫ ስፍራው ላይ መኪናዋን ወደ ደቡብ ለንደን በመውሰድ ምን ያህል ጣፋጭ ጊዜ እንዳሳለፈበት ራሱ ነበር የተናገረው።

ክስተቱ የደረሰበት የአሁኑ የስቶክ ሲቲ ተጭዋች የሆነውን ከሰማ በኃላ በመገረም ስሜት ውስጥ ሆኖ ማመን እንዳልቻለ ገልፆአል።

"የሆነ ሰው መኪናዬን ከሰረቀ በኃላ የራሱን ሙዚቃ በመክፈት እና እዛው ፍቅረኛውን በመቅጠር ተዳርቶባታል።"

ሲል ሁኔታውን እያስታወሰ ተናግሯል ..
"የራሱን ሙዚቃ ማጫወቻ CD እንኳን እዛው ትቶት ነበር። ድምፁን ጨምሮ ቆንጆ ሙዚቃውን እንደከፈተ" መኪናዋን ትቷት ሄዷል" ሲል ሁኔታውን አብራርቷል።
(ምንጭ፦ BBC Podcast)

FA IS HAPPY WITH THEIR DECISION

የፕሪሚየር ሊጉ አስተዳዳሪ ሰዎች አንቶኒ ቴይለር የመጀመሪያውን የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ እንዲዳኝ የወሰኑነት ውሳኔ ላይ ደስተኞች ናቸው።

አንዳንድ የሲቲ ደጋፊዎች ግን ግለሰቡ የተወለዱት ከኦልትራፎርድ ስቴዲየም ስድስት ማይልስ ብቻ ርቀት ላይ በምትገኘው የWythenshawe ስፍራ በመሆኑ ታይለር ለማን.ዩናይትድ እንዳያደሉ በሚል ስጋት ስለገባቸው የመሃል ዳኛውን መመደብ ከሰሙ በኃላ ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ቢገኙም FAው ግን ውሳኔአችን ትክክለኛ እና ተገቢ ስለሆነ ምደባውን አንቀይርም የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።
(ምንጭ፦ Sky Sports News)

No comments:

Post a Comment