ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Sunday 4 November 2018

እሁድ ምሽት የወጡ ከ25 በላይ የዝውውር እና ሌሎችም ዜናዎች አስተያየቶች


♦  ባርሴሎናዎች የቼልሲውን መሃል ተከላካይ ዴቪድ ሉዊዝ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ሊያዛውሩት አስበዋል። የ31 አመቱ ተከላካይ በሲዝኑ መጨረሻ ላይ ኮንትራቱ የሚጠናቀቅ ይሆናል።  (ምንጭ - Sunday Express)

.

♦  አሮን ራምሴይ ሳይታሰብ ወደ ባየር ሙኒክ ሊዛወር ይችላል። የቡድንደስሊጋው ግዙፍ ክለብ በቀጣዩ ክረምት ላይ ዌልሳዊውን ተጫዋች ለማዛወር አቅደዋል።  (ምንጭ - Sunday Express)

.

♦  ዴቪድ ደ ሂያ አዲስ ኮንትራት ለመፈረም አሁን ከሚያገኘው ሳምንታዊ የ£175,000 ደሞዝ ወደ £300,000 እንዲያድግለት ጠይቋል።  (ምንጭ - Mirror)

.

♦  ግራኒት ዣካ ከሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታ :

• ሜዳ ውስጥ ከነበሩ ተጭዋቾች በላይ ኳሶችን ለቡድን አጋሮቹ ፓስ አድርጓል (84/97 84ቱ የተሳኩ)
• ሜዳ ውስጥ ከነበሩ ተጭዋቾች በላይ የተሳኩ ሸርተቴዎችን ወርዷል (5/7 5ቱ የተሳኩ)
• ሜዳ ውስጥ ከነበሩ ተጭዋቾች በላይ ኳሷን መልሶ ሪከቨር አድርጓል (15)

.

♦  አያክሶች በ19 አመቱ መሃል ተከላካያቸው ማቲየስ ዲ ሊዥት ላይ የ€60m (£52.8m) ዋጋ ለጥፈውበታል። ተጭዋቹ በማን.ሲቲ፣ ባርሴሎና፣ ባየር ሙኒክ እና ጁቬንቱስ በጥብቅ ይፈለጋል።
(ምንጭ - Mundo Deportivo)

.

♦  የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች እራሳቸውን ከየሃገሮቻቸው ሊጎች በመገንጠል Super League የተባለ የአውሮፓን ትልቁ የክለቦች ሊግ ለመመስረት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አጠናክረው ገፍተውበታል። ሱፐር ሊጉ በ11 ክለቦች ሊመሰረት የታቀደ ሲሆን እነዚህ ክለቦች ከሊጉ አይወርዱም ተብሏል። ቡድኖቹም.. .

• Real Madrid
• Barcelona
• Manchester United
• Chelsea
• Arsenal
• Manchester City
• Liverpool
• PSG
• Juventus
• AC Milan እና
• Bayern Munich ናቸው።

ከ11ዱ ቡድኖች ውጪ ደግሞ አምስቱ ቡድኖችን ከፖርቹጋል፣ ሆላንድ፣ ሩሲያ እና ቱርክ የሚገኙ ክለቦችን በመጨመር ቁጥራቸውን ወደ 16 ከፍ የማድረግ ሃሳብ አላቸው። አላማቸውም ልክ እንደ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሚመስል የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦችን የሊግ ውድድር መመስረት ሲሆን ከትልልቅ ድርጅቶች የቴሌቭዥን መብት ስምምነቶችን በመፈረም እና እራሳቸውን ከየሃገሮቻቸው ሊጎች በመገንጠል በትንሽ ጨዋታ በርካታ ሚሊዮን ገንዘቦችን ገቢ ማድረግ ያለመ አውሮፓዊ ትልቅ ሊግ መፍጠር ነው።

የእንግሊዞቹ ማን.ሲቲ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ቼልሲ፣ አርሰናል እና ሊቨርፑል ይሄንኑ የEuropean Super League ለመቀላቀል ከሃሳቡ ጠንሳሾች ጋር በመቀራረብ በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት እና ድርድር አድርገዋል ሲል የEIC Network መረጃ ገልፆአል።
(ምንጭ - Football Leaks)

.

♠ እሁድ ከሰአት በኃላ ላይ የወጡ በFacebook ገፃችን 'Arifsports አሪፍ ስፖርት' ገፅ ላይ የለጠፍናቸው ዜናዎች ...

.

♦  ሪያል ማድሪዶች የማንቸስተር ሲቲውን ስፔናዊ አማካይ ብራሂም ዲያዝን የማዛወር ፍላጎት አላቸው።
(Source: MARCA)

.

♦  ማንቸስተር ሲቲዎች ባለፈው አመት ሊዮኔል ሜሲ አዲስ ውል በባርሴሎና ከመፈረሙ በፊት የውል ማፍረሻ ሂሳቡን £250m ከፍለው ወደ ኢትሃድ ሊያዛውሩት ሞክረው ነበር። (Source: Mundo
Deportivo)

.


♦  ማንቸስተር ዩናይትዶች ለዴቪድ ደሂያ እና ለአንቶኒ ማርሻል ሊያቀርቡላቸው ያሰቡት አዲስ ኮንትራት ውል በአሌክሲስ ሳንቼዝ ሳምንታዊ £400,000 ደሞዝ ሳቢያ እየተጓተተ ነው። የቺሊያዊው ደሞዝ ከነሱ ጭማሪ ጋር ሲሰላ የክለቡን የፋይናንስ ምጣኔ ያናጋል ተብሏል።  (Source: Sunday Mirror)

.

♦  Official: ሉካስ ቶሬራ በትላንት ምሽቱ የአርሰናል እና ሊቨርፑል ጨዋታ ላይ ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ ሳቢያ የጨዋታው ኮከብ በሚል ተመርጧል።
(BT)

.

♦  የርገን ክሎፕ : "አርሰናሎች አሁንም አደረጉት! ሁሉንም አጥቂዎቻቸውን ቀይረው አስገቡ። ሮበን ቫንፐርሲ እና ቤርካምፕም ይገቡ ይሆን ብዬ ጠብቄ ነበር" -  ሲሉ የርገን ክሎፕ መድፈኞቹ ነጥብ ለመጋራት ወደ ሜዳ ያስገቧቸው ተጭዋቾች እንዳስገረሟቸው ተናግረዋል።  (LynchStandard)

.

♦  ቶማስ ሙለስ: "አሁን በአራት ነጥቦች ከመሪው ርቀናል። እርግጥ ነው ወደ ሊጉ ሰንጠረዥ አናት ላይ መመለስ እንፈልጋለን። እንመለሳለንም። ለዛም እርግጠኛ መሆን ትችላላቹ" - ባየር ሙኒክ ትላንት በሜዳው ነጥብ መጣሉ ይታወሳል።  (Bild)

.

♦  ኡናይ ኤምሬ እንደሚሉት ከሆነ አርሰናሎች ሊቨርፑልን ለማሸነፍ ጥቂት እድል ያስፈልገን ነበር ብለዋል። አሰልጣኙ እንሳሉት ከሆነም ከመሪዎቹ ጋር ያላቸውን ልዩነት እያጠበቡ እንደመጡ ያምናሉ።

“የዛሬው ጨዋታ ለኛ ጥሩ ፈተና ነበር። አሁንም እንደዚህ አይነት ፈታኝ ጨዋታዎች ያስፈልጉናል። የጨዋታው ድባብና መንፈስ ልክ እኛ እንዲሆን የምንፈልገው አይነት ነው"  (liverpoolecho)

.

♦  የርገን ክሎፕ እንዳሉት ከሆነ በEuropean Super League ሃሳብ ላይ እንደሚደግፉት በቀልድ መልክ ተናግረዋል። "እንደተባለው ሱፐር ሊጉ እውን የሚሆን ከሆነ ጥቂት ጨዋታ ብቻ እናደርጋለን፤ በርካታ ብሮችንም እናገኛለን። ስለነገሩ ምንም አላሰብኩበትም። ግን ጥሩ ሃሳብ ይመስለኛል የሚደገፍ ነው። ጥቂት ጨዋታ አድርገህ ብዙ ብር ማግኘት ደስ እሚል ሃሳብ ነው"   (skysports)

.

♦  ፓብሎ ዛባሌታ የአሰልጣኝነት ባጁን ከደሰደ በኃላ ማንቸስተር ሲቲን ወደፊት እንደሚያሰለጥን ሲጠየቅ፦
"ለምን አይሆንም? በሲቲ ዘጠኝ አመታትን አሳልፌአለው። ልክ እንደ ቤቴ ያህል ነው። ባለፈው ከካልዶን ጋር ባደረግነው ውይይት ክለቡ በሩ ለኔ ሁሌም ክፍት እንደሆነ ነግሮኛል። መመለስ ለኔ ልዩ ስሜት አለው ለወደፊት የሚሆነውን እናያለን"

.

♦  ማውሪዚዮ ሳሪ እንዳሉት ከሆነ ቼልሲን በአውሮፓ እና በእንግሊዝ ውድድሮች ላይ ስኬታማ ማድረግ ካስፈለገ ተጭዋቾችን በተለያዩ ተደራራቢ ጨዋታዎች ላይ በማፈራረቅ ማጫወት እንደሚኖርበት ተናግሯል።  (MailSport)

"ሁሉንም ውድድሮች መመልከት አለብን። በሊግ ካፕ፣ ዩሮፓ ሊግ እና በኔሽንስ ሊግ የሚደረጉ ጨዋታዎችን ሁሉ ማሰብ አለብን። ስለዚህ ማፈራረቅ ጥሩ መፍትሄ ይሆናል።"

.

♦  የቼልሲው አለቃ ማውሪዚዮ ሳሪ እንዳረጋገጡት ከሆነ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው አማካያቸው ሩበን ሉፍተስ ቼክ ምንም እንኳን በቂ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ እድል ባያገኝም በጥሩ የዝውውር መስኮት ላይ ክለቡን እንዲለቅ አይፈቀድለትም።   (IntChampionsCup)

.

♦  ጂያንሉጂ ቡፎን በPSG ያለውን ኮንትራት እንደሚያራዝም ይጠበቃል። ግብ ጠባቂው ኮንትራቱን የሚያራዝም ከሆነ እስከ 42 አመቱ ድረስ መጫወቱን የሚቀጥል ይሆናል።
(Source: Le Parisien)

.

♦  ማንቸስተር ዩናይትዶች ፊል ጆንስን ለተጨማሪ 12  ወራት ውሉን የማራዘም አማራጫቸውን ተጠቅመው አዲስ ውል ያቀርቡለታል። ሆኖም ለተከላካዩ በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ፈላጊ ክለቦች ካሉ ክለቡ ጥያቄውን ያደምጣል።   (Metro)

.

♦  ጆዜ ሞሪንዎ : “ደጋፊዎች ‘attack attack
attack’, እያሉ የሚዘምሩትን መዝሙር እወደዋለው። ሆኖም ቡድንህ መርጋት አለበት። ወጥ የሆነ አቋም ዛሬም አላሳየንም" (BT)

.

♦  የሰድሞው የስፐርስ ተጫዋች ሚዶ እንዳለው ከሆነ ቶተንሃም ሆትስፐሮች ሁሌም ቢሆን ከተፎካካሪዎቻቸው በላይ የሚጠበቁ ግን በታች ውጤት የሚያመዘግቡ ሆነዋል ብሎ ያምናል። ስለዚህ የዋንጫ ተፎካካሪ ናቸው ብሎ አያምንም።

"ላሁኑ ቶተንሃሞች የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ያነሳሉ የሚል እምነት የለኝም"   (5LiveSport)



No comments:

Post a Comment