ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Wednesday 7 November 2018

ማክሰኞ ምሽት የወጡ ከ25 በላይ የዝውውር እና ሌሎችም ዜናዎች

ግራኒት ዣካ የፈረንጆች አዲስ አመት ከገባ ጊዜ ጀምሮ ብናሰላ ፕሪሚየር ሊጉ በተደረገባቸው 49 ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍ ከ3ት ተጭዋቾች ጋር ሪከርዱን ተጋርቷል። የሌስተር ሲቲው ሃሪ ማጉዌይር እና የበርንማውዙ ናታን አኬ የቀሩት ብዛት ጨዋታ ያደረጉ ተጭዋቾች ሆነዋል። (ምንጭ: Squawka)

.

ፍሌቸር ስለ ቀጣዩ የማንቸስተር ደርቢ ጨዋታ: "ዩናይትዶች ለጨዋታው ልክ አምና በሁለተኛው ዙር በገጠሟቸው ሙድ መግባት አለባቸው። ሲቲዎች ለረጅም ግዜ ኳሱን መቆጣጠራቸው አይቀርም። ለዚህ በመልሶ ማጥቃት ጥሩ ኳስ መስርተው ወደፊት መሄድ ይጠበቅባቸዋል

"ራሽፎርድ ቄሚ አሰላለፍ ውስጥ ቢገባ መልካም ነው። ሉካኩ ይግባ አይግባ በሚለው ላይ መወሰን ይከብደኛል። ሳንቼዝ፣ ራሽፎርድ እና ማርሻል ከፊት ከሆኑ ጨዋታው ፍሰት ይኖረዋል። የሲቲ ተከላካዮችን ስጋት ላይ ሊጥሉ ይችላሉ"

.

ካይል ዎልከር ስለ ማንቸስተር ደርቢው: "በስቴዲየሙ የሚኖረውን ቆንጆ ድባብ መፍጠር የምንችለው እኛ ተጭዋቾች ራሳችን ነን። ደጋፊዎቹ ዘና እንዲሉ ማድረግ አለብን። እነርሱ ለኛ 12ተኛ ተጭዋቾች ማለት ናቸው። ጨዋታውን አሸንፎ ለመውጣት ከባድ ስራ ይጠብቀናል። ለክለቡ የሆነ ታሪክ የመስራት ፍላጎታችን ከፍተኛ ነው"

.

ብራዚላዊው እውቅ ጋዜጠኛ በደቡብ አሜሪካ የሊቨርፑል ክለብ መልማይ ሆኖ መቀጠሩን በይፋ ገለፅ። ዳስለር ማርኩዌንስ ለብራዚሉ እውቅ የህትመት ውጤት UOL አምደኛ ሆኖ በመፃፍ የሚታወቅ ሲሆን በድንገት የስራ ለውጥ ማድረጉን ገልፆአል።    (ምንጭ: liverpoolecho)

"አሁን ከጋዜጠኝነት የማመልጥበት ወቅት ነው። አዲስ ነገሮችን የምማርበት አዲስ ነገር የማልምበት እና አዳዲስ ጓደኞችን የማፈራበት ጊዜ ላይ እገኛለሁ። አሁን የሊቨርፑል ክለብ የብራዚል እና ላቲን  ተጭዋቾች መልማይ ሆኛለሁ"  - ሲል ያልተጠበቀውን የስራውን ለውጥ ይፋ አድርጎታል።

.

ኮቫች ስለ ሊሳ ሙለር[የአሰልጣኙን ተጭዋቾች አመራረጥ እና አጨዋወት በመቃወም ምስል ያጋራችው የቶማስ ሙለር ባለቤት] በInstagram ስለፖሰተችው ተጠይቀው: "እኔ በየነገሩ ቂም የምቋጥር በቀለኛ አይደለውም። ልታምኑኝ ትችላላችሁ አሁን አርዕስቱ ተዘግቷል"


➦  አንቶኒ ታይለር በሳምንቱ መጨረሻ በኢትሃድ ስቴዲየም የሚደረገውን የማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ጨዋታ በዋና ዳኝነት እንዲመሩት ተመርጠዋል።

.

ቼልሲዎች በዌስትሃም ቤት አዲስ የቀረበለትን ኮንትራት አልቀበልም በማለት ከክለቡ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባውን ታዳጊ ባለተሰጥዎ ዲክላን ሪሴን ለማዛወር ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተሉት ይገኛል ሆኖም ከቶተንሃሞች ፉክክር ይጠብቃቸዋል።
(ምንጭ ፦ 90min)

.

ሪያል ማድሪዶች ከAdidas ጋር የአለም ሪከርድ የሆነ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ውል ተፈራርመዋል። በዚህ መሰረት ውሉ ለቀጣዮቹ 10ት አመታት የሚቆይ ሲሆን የ£950 ሚሊዮን ፓውንድ ክፍያ በማግኘት በእግርኳስ ታሪክ ትልቁን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ውል አግኝተዋል። ከዚህ በፊት ማን.ዩናይትዶች ከአዲዳስ የሚከፈላቸው የ£750m ሪከርድ ሆኖ ቆይቷል።  (ምንጭ: Daily Mirror)

.

ማርክ ሂውጅ የፊታችን ቅዳሜ ከዋትፎርድ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ የማያሸንፉ ከሆነ ከሳውዛምፕተን ስራቸው ይሰናበታሉ። ሳም አላርዳይስ እና ዴሺድ ሞዬስ ሊተኳቸው ይችላሉ።
(ምንጭ: Mirror)

.

ኤሲ ሚላኖች የማንቸስተር ዩናይትዱን መሃል ተከላካይ ኤሪክ ቤይሊን ለማዛወር ጥያቄ ሊያቀርቡ ነው። ተከላካዩ በጆዜ ሞሪንዎው ቡድን ውስጥ በቂ የመሰለፍ እድል እየተሰጠው ባለመሆኑ ግራ ተጋብቷል።  (ምንጭ: ESPN)

.

ሞሪሲዮ ፖቸቲንዎ ወደ ሳንቲያጎ በርናባው እንሲዛወሩ ክለቡ እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲረሱት ለስፔኑ ክለብ ሰዎች ነግረዋቸዋል። በቶተንሃም እንደሚቆዩም አሳውቀዋቸዋል።   (ምንጭ: Sun Sport)

.

ቼልሲዎች የ£45 ሚሊዮን ዋጋ የተተመነውን ጆአዎ ፌሊክስ ለማዛወር እያደረጉት ያለው ፈጣን እንቅስቃሴ ሳንካ ገጥሞታል። ምክንያቱ ደግሞ ቤኔፊካዎች በክለቡ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ሊያስፈርሙት በመቃረባቸው እና በውሉ ላይ የ£105 ሚሊዮን መልቀቂያ አንቀፅ ሊያካትቱበት ስላሰቡ ነው።  (ምንጭ: Daily Mirror)

.

ማንቸስተር ዩናይትዶች የጁቬንቱሶቹን ተከላካዮች መሃዲ ቤናሺያ፣ አሌክስ ሳንድሮ እና ጆአዎ ካንሴሎ የማዛወር ፍላጎት አላቸው።  (ምንጭ: Tuttosport)

.

ባርሴሎናዎች የቼልሲውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ዊሊያንን ለማዛወር የነበራቸውን ፍላጎት በድጋሚ ቀስቅሰውታል። የስፔኑ ሻምፒየን ክለብ ተጭዋቹን በጥር የዝውውር መስኮህ ላይ ለማዛወር ከወኪሎቹ ጋር ከወዲሁ ንግግር ማድረግ ጀምረዋል።
(ምንጭ: La Sexta)

.

በማርኮ ቬራቲ እና PSGዎች ነካከል ሲደረግ የቆየው አዲስ ውል ስምምነት ድርድር በድጋሚ ተቋርጧል። በመሆኑን ሁኔታውን በቅርበት ሆነው ሲከታተሉት የቆዩት ጂቬንቱስ፣ ናፖሊ እና ኢንተር ሚላኖች የ26 አመቱን ኮከብ ለማዛወር ፉክክር ያደርጋሉ።
(ምንጭ: Calciomercato)

.

ማንቸስተር ዩናይትዶች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ላይ ለኢንተር ሚላኑ ተከላካይ Milan Škriniar ዝውውር የ€75 ሚሊዮን ሂሳብ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ኢንተሮች ከ€80m-€100m ድረስ  እንዲከፍሏቸው ጠይቀው ውድቅ አድርገውባቸዋል። (ምንጭ: fcinternews)

.

አርሰን ዌንገር ወደ አሰልጣኝነቱ ለመመለስ ተቃርበዋል። የቀድሞው የአርሰናል አለቃ ከኤሲ ሚላን አሰልጣኝነቱ ሊሰናበት የተቃረበውን ጄናሮ ጋቱሶ ለመተካት ከክለቡ ጋር ጥልቅ ድርድር እና ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው።  (ምንጭ: Mirror via Football France)




No comments:

Post a Comment