ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Friday 26 October 2018

ኦዚል ለግራም ሶነስ ምላሽ ሰጥቷል፤ የማን.ዩናይትድ ተጭዋቾች አምፀዋል እና ኔይማር በቡድን አጋሩ ታክል ተገብቶበታል



ኔይማር በራሱ ቡድን ተጭዋች ጎል እንዳያስቆጥር ታክል ከተገባበት
PSGዎች በከትላንት በስቲያ በሻምፒየንስ ሊጉ ናፖሊ ጋር 2ለ2 በመለያት አቻ ከተለያዩ በኃላ ኔይማር ማንንም ለመጩበጥ ፍቃደኛ አልነበረም፤ አሰልጣኙንም አልጨብጥም ብሏል። የውሃ ፕላስቲኩን በንዴት እየጠለዘ ሜዳውን ለቆ በቀጥታ ወደ መልበሻ ክፍል አመራ አንጀል ዲ ማርያ በ93ተኛው ደቂቃ ላይ PSGዎችን አቻ ያደረገች ጎል አስቆጥሮ የቡድኑ ተጭዋቾች እና አሰልጣኙ ፍፁም ደስታ ፈንጠዝያ ላይ የነበሩ ቢሆንም ብራዚላዊው ኮከብ ኔይማር ግን በንዴት የሜዳውን ሳር በእግሩ እዶለ ወደ መልበሻ ክፍል ሲገባ ታይቷል። ብራዚላዊውን ኮከብ ያናደደው ነገር የተከሰተው ገና ጨዋታው በተጀመረ 2 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሲሆን ከኮርና አካባቢ የተሻገረለትን ኳስ ጥሩ ኳስ ኔይማር በቀኝ እግሩ ለግቶ ከመረብ ሊዶላት ሲል የቡድን አጋሩ ኡራኅዊው አጥቂ ኤዲሰን ካቫኒ ግን ከፊቱ በሸርተቴ በመውረድ ኳሷን በአግባቡ እንዳይመታ ያጨናገፈበት ሲሆን ኔይማርም መጠነኛ ህመም ተሰምቶት ሜዳ ላይ ወድቆ ለህክምና ለግዜው ለመውጣት ተገዶ ታይቷል። ክስተቱ እንግዳ ነገር በመሆኑ በርካቶች ተነጋግረውበታል። በሁኔታው ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ ብስጭቱን የገለፀው ኔይማር ማንንም ሳያናግር ቶማስ ቱቸልንም ሳይጨብጥ ወደ መልበሻው ክፍል በማምራት በካቫኒ ድርጊት መበሳጨቱን በተግባር አሳይቷል። ከዛ በኃላ ስለሁኔታው ኡራጓዊው አጥቂ ያለው ነገር ባይኖርም ክስተቱ ግን የሁለቱን ተጭዋቾች የርስ በርስ ግንኙነት ወደባሰ ቀውስ ውስጥ የከተተ ነው ተብሏል። ተጭዋቾቹ አምና ቅጣት ምት ማን ቀድሞ ይምታ በሚል ሜዳ ላይ ተጋጭተው እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

የማንቸስተር ዩናይትድ ተጭዋቾች አመፅ ላይ ናቸው! ለምን?

የማንቸስተር ዩናይትድ ኮከቦች ክለቡ ከልምምድ በኃላ እንደሁልግዜውም የሚያደርገውን የስፓንሰሮች ሃላፊነት የመወጣት ተግባር በመቃወም አመፅ ጀምረዋል ሲል TheSun ጋዜጣ ዘገበ። በኦልትራፎርድ የነገሰው ስጋት አሁንም የቀጠለ ሲሆን የተከፉ አንዳንድ የማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች የስፖንሰሮችን ተግባራት ለክለቡ አንሳተፍ በማለት የክለቡን የሜዳ ላይ ችግር ከሜዳ ውጪም እንዲባባስ እያደረጉ ናቸው። MailOnline ጋዜጣን ጠቅሶ ዘሰን እንደዘገበው ከሆነ በርካታ የዋናው ቡድን ተጭዋቾች ክለቡ ትላንት ለነበረበት የንግድ አጋሮች ሃላፊነት ተግባር መገኘት ይጠበቅባቸው ነበር። አሽሊ ያንግ፣ ሊ ግራንት፣ ማርከስ ራሽፎርድ እና ፖል ፖግባ በቦታው በመገኘት ቃለ መጠይቅ አድርገው የ True Religion Manchester United press ይፋ ሲደረግ ተሳትፈዋል። ሆኖም ሌሎች መገኘት የነበረባቸው ተጭዋቾች ግን በቦታው ሳይገኙ ቀርተዋል። በየወሩ በማን.ዩናይትድ የአዎን ልምምድ ማዕከል ስፖንሰሮች በአካል በመገኘት ከቡድኑ ተጭዋቾች ጋር ፎቶ እና ቪዲዮዎችን የመውሰድ ስምምነት አላቸው። ሆኖም ይሄንን ተግባር ትላንት ለመፈፀም ፍቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። በስፍራውም አልተገኙም። ከተጭዋቾቹ ባሻገር አሰልጣኙ ጆዜ ሞሪንዎ ሳይቀሩ በsponsorship event ላይ አለመገኘታቸው ነው የተነገረው።

ሜሱት ኦዚል ለግራም ሶነስ ትችት አስገራሚ ምላሹን ሰጥቷል

'ከመሳቅ ውጪ ምን እላለሁ' ሲል የአርሰናሉ ኮከብ የስካይ ስፖርት ተንታኝ የሆኑት ግራም ሶውነስ ትችት ላይ ምላሹን ሰጥቷል ሶውነስ እንዳሉት ከሆነ ቡድኑ ሌስተር ሲቲን ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ ጀርመናዊው ጥሩ እንቅስቃሴ ቢታሳይም 'ጨዋታው ላይ የለም ነበር' ማለታቸው አስገርሞታል። አርሰናሎች በድንቅ የቡድን እንቅስቃሴ ሌስተር ሲቲዎችን 3ለ1 ከረቱበት ጨዋታ በኃላ ግራም ሶውነስ ስለ 29 አመቱ ጀርመናዊ ኢንተርናሽናል ተጭዋች ኦዚል 'በአብዛኛው የጨዋታው ክፍል ላይ ይጠፋ ነበር' ሲሉ አስተያየት ሰጥተውበት ነበር። ሆኖም ኦዚል እንዲህ በማለት ምላሹን ሰጥቷቸዋል። "ሰምቼው ስቄያለሁ" ሲል ስለ ሶውነስ ሳይሆን ስለ አሰልጣኙ ብቻ እንደሚጨነቅ ተናግሯል። እንደ ሶውነስ ያሉ ተቺዎቹ ላይ ምን አይነት ምላሽ እንዳለው ሲጠየቅ ኦዚል ለSky Sports እንዲህ ብሏል: "አስቆኛል። እኔኮ ካሁን በኃላ ወጣት እየሆንኩ አልሄድም። ፕሮፌሽናል እግርኳስ መጫወት የጀመርኩት በ16 ወይም 17 አመቴ ላይ ነው። "ነገሮች ሁሌ ቀና አይሆኑልህም። መውጣትም መውረድም ያጋጥምሃል። አንዳንዶች ይወዱሃል አንዳንዶች ደግሞ ይጠሉሃል" "ዋናው አስፈላጊው ነገር ግን አሰልጣኙ እኔን መርዳት መቻሉ ነው። ስህተት የምሰራ ከሆነ እሱ ይነግረኛል። ከርሱ ጋር ማውራት እንችላለን፤ ስህተቴን ለቀጣዩ አርመዋለሁ" "ሆኖም ሰዎች ዝም ብለው የጋዜጣ ሽፋን ለማግኘት ሲሉ ስለኔ መጥፎ አስተያየት ቢሰጡ እሱ እኔን አያስጨንቀኝም። "ሁሌም ቢሆን እግር ኳስን የምጫወተው በታላቅ ተነሳሽነት ነው። ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ እፈልጋለሁ - በልምምድ ላይ እንኳን ብሆን ሽንፈትን እጠላለሁ" ሲል ለሶውነስ ትችት ምላሹን ሰጥቷል።

No comments:

Post a Comment