ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Wednesday 7 November 2018

እሮብ ከሰአት በኃላ የወጡ ያመለጧችሁ ልዩ ዜናዎች - News You Missed Today

KYLIAN MBAPPE'S በፒ.ኤስ.ጂ ክለብ ለመቆየት የጠየቀው አስገራሚ ደሞዝና ጥቅማ ጥቅም ይፋ ሆነ። ተጭዋቹ የBallon d'Or ሽልማትን የሚያሸንፍ ከሆነ ከኔይማር ደሞዝ በላይ እንዲከፈለው ይፈልጋል።


ታዳጊው ባለተሰጥዎ ሞናኮን በመልቀቅ የፈረንሳዩን ሃብታም ክለብ ፒ.ኤስ.ጂን ባለፈው አመት በውሰት ከተቀላቀለ በኃላ በክረምቱ በቄሚ ዝውውር ለክለቡ ፊርማውን አኑሮአል።

እናም በፒ.ኤስ.ጂ የሚያቆየውን ውል ለመፈራረም የ19 አመቱ ኮከብ በአምስት አመታት የክለቡ ቆይታው አመታዊ የ£48 million ደሞዝ ከግብር በኃላ እንዲሰጠው ጠይቋል።

እንደ Football Leaks, ዘገባ ከሆነ የቀድሞው የሞናኮ ኮከብ ምባፔ በመላው አለም ያለ ደጋፊዎች ግርግርና ምንም መጨናነቅ፣ መጉላላት ሳይደርስበት ከደጋፊዎች ትኩረት በማምለጥ ከአንድ ሃገር ወደ ሌላ ሃገር እንደልቡ የሚጓዝበትን የግል ጀት ክለቡ እንዲመድብለትም ጠይቋል።

ሆኖም PSGዎች ይሄንን ሁሉ ጥያቄዎቹን ውድቅ በማድረግ ለተጭዋቹ የተለያዩ ወጪዎች መሸፈኛ ይሆን ዘንድ በወር £27,000 ቦነስ ክፍያ በመስጠት፣ ተንከባካቢ፣ ሹፌር እና ቦዲጋርድ መድበውለታል።

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ታዳጊው የባለንደኦር ሽልማትን የሚያነሳና የአለማችን ምርጡ የሚባል ከሆነ ከኔይማው ደሞዝ ሳምንታዊ £600,000 በላይ ደሞዝ እንዲከፈለው ጠይቆ ተስማምቷል።

________________________________________

●  ማንቸስተር ዩናይትዶች ጋሬዝ ቤልን ከሪያል ማድሪድ ለማዛወር የ£100 million ክፍያ ለማቅረብ አስበዋል። ምክንያቱ ደግሞ የሪያል ማድሪድ ተጭዋቾች ዌልሳዊው አጥቂ ከሳንቲያጎ በርናባው እንዲሰናበት በመፈለጋቸው ነው።


ዌልሳዊው ኮከብ ፕሪሚየር ሊጉን በ86 ሚሊዮን ውፓንድ ከለቀቀ ከ2013 ጀምሮ ወደ እንግሊዝ ይመለሳል በሚል ተደጋጋሚ ወሬ ሲናፈስ ነበር።

ታዋቂው ስፔናዊ ጋዜጠኛ Eduardo India ለTV show El Chiringuito እንዳለው ከሆነ የሪያል ማድሪድ ነባር ተጭዋቾች ሰርጂዎ ራሞስን ጨምሮ ለክለቡ ውጤት ማጣት ምክንያቱ ጋሬዝ ቤል መሆኑን ለቸርማኑ ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ነግረዋቸዋል።

ቤል በቅዳሜው የቫላዶሊድ ጨዋታ ላይ ቡድኑ 0-0 እያለ ደጋፊዎች ሲጮሁበት የተሰማ ሲሆን በርሱ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ብራዚላዊው ታዳጊ ከገባ በኃላ ቡድኑ መነቃቃትን አሳይቶ 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፎ እንዲወጣ ማድረግ ችሏል።

________________________________________

●  ALEXANDRE LACAZETTE'S ሜዳ ውስጥ እያሳየ ካለው ድንቅ እንቅስቃሴ እና ጎል ከማስቆጠር ሚናው ባሻገር ከሜዳ ውጪ ማቲዎ ጉንዶዚ እያሳየ ላለው ድንቅ ብቃት ምክንያት እንደሆነ ተሰምቷል። ላካዜቲ ተጭዋቹ በእንግሊዝ በፍትነት እንዲለመድ ከጎኑ በመሆን ድጋፍ እንደሚያደርግለት ተሰምቷል።


________________________________________

●  WENGER TO REAL MADRID?


ARSENE WENGER በሪያል ማድሪድ የሚፈለጉ ከሆነ የሚቀርብላቸውን ጥያቄ ላለመቀበል እንደሚቸገሩ ተገለፀ። ይሄንን ያለው የSunSport ፀሃፊ ማርቲን ሊፕቶን እንደሚለው ከሆነ አርሰን ዌንገር የሎስብላንኮዎቹ አለቃ ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ትልቁን መርከብ እንዲሾፍሩት ከሚፈልጎቸው ሰዎች መሃከል አንዱ ናቸው።


ትላንት ምሽት ዜና ካላነበባችሁት ፦ ማክሰኞ ምሽት የወጡ ከ25 በላይ የዝውውር እና ሌሎችም ዜናዎችን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ


________________________________________

●  WEST HAM ዩናይትዶች የቼልሲውን ሩበን ሉፍተስ ቼክ ለማዛወር የነበራቸውን ህልም ማውሪዚዎ ሳሪ ተጨናፍጎባቸዋል።


መዶሻዎቹ ተጭዋቹን በጥር የዝውውር መስኮት ላይ እንደሚያስፈርመት እርግጠኞች የነበሩ ቢሆንም በአለም ዋንጫው ላይ ለቡድኑ ድንቅ እንቅስቃሴ ያደረገውን ተጭዋች ሳሪ ለጉረቤት ተቀናቃኝ ክለብ አሳልፈው መስጠት አልፈለጉም።

እንደ Daily Mirror ዘገባ ከሆነ የዌስትሃሙ አለቃ ማኑኤል ፔሌግሬኒ ሌላኛውን የለንደን ክለብ በውሰት ውል በጥር እንዲሻገር ለማድረግ ቢጥሩም የ22 አመቱን ተጭዋች ሳሪ አለቅም በማለታቸው በስታምፎርድ ብሪጅ መቆየቱ እርግጥ ሆኑአል።

No comments:

Post a Comment