ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Friday 2 November 2018

አርብ ምሽት የወጡ የዝውውር እና ሌሎች ዜናዎች



➦  አርሰልናል፣ ዶርትመንድ፣ ኢንተር ሚላን፣ ናፖሊ እና ሮማ የሪያል ማድሪዱን ታዳጊ ቪኒሺየስ ጁኒየር በጥር የዝውውር መስኮት ላይ በውሰት ውል የማዛወር ፍላጎት አላቸው።   (Source: Don Balon)

.

➦  ፋቢንዎ ሊቨርፑልን በተቀላቀለ ገና በ6ተኛው ወር ላይ ክለቡን በመልቅ ወደ ፓሪሱ ክለብ ፒኤስጂ ሊያመራ ይችላል ተባለ። ምክንያቱ ደግሞ በአንፊል በቂ የመሰለፍ እድል ስላልተሰጠው 'በመሰላቸቱ' ነው።  (Source: Le Parisien)

.

➦  የማንቸስተር ሲቲው ኮከብ ኬቨን ዲ ብርየን በደረሰበት የጉልበት ጉዳት ሳቢያ ከ5-6 ሳምንታት ያህል ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ አስታውቋል። ጉዳቱ ቀዶ ጥገና የማያስፈልገው ሲሆን ቤልጂየማዊውን አማካይ ከማንቸስተር ደርቢ ጨዋታው ውጪ አድርጎታል።  (Citywatch)

.

➦  ጆዜ ሞሪንዎ ሮሚዮ ሉካኩ ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ይገባ አይገባ ይሆን ተብለው ሲጠየቁ የመለሱት፦

"ሉካኩ ይሰለፋል አይሰለፍም የሚለውን ለማወቅ ሳሙኤልን ጠይቁት(ቡድኑ ከቼልሲ ጋር ከመጫወቱ በፊት የዩናይትድን ቋሚ አሰላለፍ መረጃ ከጨዋታው ቀድሞ በማውጣት Leaked አድርጓል የተባለው የMEN ጋዜጣ ፀሃፊ ነው)" - በሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

.

➦  ቼልሲዎች አሮን ራምሴይን ለማዛወር ያላቸውን ፍላጎት በድጋሚ በማጤን ከዝውውሩ ፉክክር ራሳቸውን ሊያርቁ አስበዋል። ምክንያቱ ደግሞ ሮዝ ባርክሌይ እና ሩበን ለፍተስ ቼክ አሁን በክለቡ እያሳዩ ያሉት ድንቅ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው።
(Source: Daily Star)

.

➦  ቲየሪ ሆነሪ የአርሰናሉን ታዳጊ ባለተሰጥዎ ኢምሌ ስሚዝ ሮዌ ወደ ሞናኮ ማዛቀር ይፈልጋል።
(Source: Daily Star)

.

➦  ኢምሬ ስለ ጉንዱዚ: "እንደማስበው እርሱ እኔ በምፈልገው የጨዋታ መንፈስ በመጫወት ላይ ያለ ልጅ ነው። በሁሉም ጨዋታዎች ላይ ያለውን ተነሳሽነት ተመልከቱ። በጨዋታ ላይ ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት አላየሁም ጨዋታውን ይቆጣጠራል። የሚጫወትበት መንገድ ሁሌም ለውጤት የተራበ ነው፤ ቀይ ካርድ መመልከት የጨዋታው አንድ አካል ነው"

.

➦  ሊቨርፑሎች ለጆ ጎሜዝ አዲስ ኮንትራት ሊሰጡት አስበዋል። ተጭዋቹ ጥሩ ብቃት ላይ ሲሆን በአዲስ ውሉ ዙሪያ ከክለቡ ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሯል። የአንፊልድ ሰዎችም የ21 አመቱን መሃል ተከላካይ ተጭዋች በክለቡ የሚያቆየውን ውል በቀናት አሊያም በሳምንታት ውስጥ እንደሚያስፈርሙት ተማምነዋል።  (mirror)

.

➦  ሞሃመድ ሳላህ ወደ ሊቨርፑል ለመዛወር የነበረው ምኞት ገና ከዛሬ 6 አመታት በፊት የትውልድ ሃገሩን ግብፅ ለቆ ወደ ባዜል ሲዛወር የነበረው ህልም ነው።

"በምጫወትበት የPlayStation ጌም ላይ የሊቨርፑልን ክለብ እመርጥ እንደነበር የተወራው እውነት ነው። አንዳንዴ ሌላ ቡድን ልመርጥ እችላለሁ በብዛት ግን ሊቨርፑል ነበር ምርጫዬ"
(skysports)

ሳላህ መናገሩን ቀጥሏል: “ከግብፅ ወደ ባዜል ሳመራ አንድ ቀን ወደ ሊቨርፑል እንደምዛወር ህልም ነበረኝ። ያኔም ለክለቡ የመፈረም እድል ነበረኝ ሆኖም ለሁለቱም ክለቦች እንዳሰቡት ዝውውሩ አልተሳካም"

.

➦  እንደ አርሰናሉ ሰው ጋዚዲ እምነት ከሆነ አሮን ራምሴይ ከክለቡ የመክፈል አቅም በላይ የሆነ ትልቅ ደሞዝ ጠይቋል። ሆኖም ሊከፍሉት አስበው ነበር። ሳይታሰብ ኢቫን ወደ ኤሲ ሚላን ሲሄዱ ነገሮች ተገለባበጡ። የክለቡ ነባር አስተዳደሮች እና ኡናይ ኤምሬ ተነጋግረው ሊከፈለው የታሰበው ረብጣ ገንዘብ እንሰማይገባው ተስማምተው እቅዱን ሰረዙት።  (Telegraph)

.

➦  አርሰን ዌንገር የቀድሞ ክለቡ የሊጉን ዋንጫ ያነሳ እንደሆን ሲጠየቁ: “ለምን አይሆንም? ያለፈው አመት ሪከርዶቻችንን ከተመለከታችሁ በሜዳችን 15 ጨዋታዎችን አሸንፈናል። ጥሩ ያልነበርነው ከሜዳ ውጪ ስንጫወት ነው። ሆኖም አሁን ጥራቱ አለ አርሰናል እድል አለው"

.

➦  ማኑኤል ኑዌር: "ቲያጎ አልካንትራ ቡድናችን ባደርገው በርካታ ጨዋታዎች ላይ እንድናሸንፍ ቁልፍ ሚናን ተጫውቷል። የርሱ በጉዳት መራቅ ይጎዳናል። ሆኖም ችግሩን መቋቋም መቻል አለብን"  [tz]

.

➦  ፔፕ ጋርዲዮላ ስለ ዲ ብርየን ጉዳት: "ጉዳቱ ከባድ ይሁን ምን ይሁን የምናውቀው ነገር የለም። ቤልጂየማዊው አማካይ በክለቡ ዶክተሮች ምርመራ ይደረግለትና የጉዳቱን አይነት እና መጠን የምንለይ ይሆናል።"   (Dailymail)

.

➦  ቦሩሲያ ዶርትመንዶች የማንቸስተር ሲቲውን ፊል ፎደን የማዛወር ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት አላቸው ሲል ምንጭ ተናግሯል። ተጭዋቹ ወደ ጀርመኑ ክለብ ለመዛቀር ፈቃደኛ ከሆነ ከጃዶ ሳንቾ ጋር የመሰለፍ እድል እንደሚሰጡት ቃል ገብተውለታል። አሁን ፎደን እና ወኪሉ የተፈጠረውን የአዲስ ኮንትራት ውዝግብ ለመፍታት ከክለቡ ሲቲ ጋር በመሆን በመነጋገር ላይ ይገኛሉ።   [Daily Mail]

.

➦  ዩዚያን ቦልት ለአውስትራሊያው ክለብ ሴንትራል ኮስት ማሪነርስ በፕሮፌሽናልነት ለመጫወት የነበረው ህልም ተጨናግፎበታል። በክለቡ የሙከራ ጊዜ ቢያሳልፍም ሊሳካለት አልቻለም።

"ለክለቡ አመቱ የስኬት እንዲሆንላቸው ምኞቴ ነው" ሲል ጃማይካዊው ምኞቱን ገልፆአል።
(Source: BBC)

.

➦  የብራይተኑ ግብ ጠባቂ ማት ሪያን ሳይጠበቅ የዴቪድ ደ ሂያ ተተኪ ይሆል በሚል በማንቸስተር ዩናይትዶች ክትትል እየተደረገበት ይገኛል።   (Source: Sun Sport)

.

➦  ቦሩሲያ ዶርትመንዶች ምንም እንኳን ኮከባቸውን ጃዶን ሳንቾ ለማዛወር PSGዎች ፍላጎት ቢያሳዩም የመሸጥ ፍላጎት የላቸውም።
(Source: SkySports)

.

➦  የቀድሞው የቼልሲ አለቃ አንቶኒዮ ኮንቴ አሁንም የሪያል ማድሪድ ኢላማ ውስጥ ናቸው። ምንም እንኳን ያለፉት ቀናት ላይ ኮንቴ ክለቡን አይዙም ቢባልም አሁንም የመረከብ እድላቸው አልተሟጠጠም።
(Source: AS)

.

➦  አሮን ራምሴይ በሁለቱ የጣሊያን ግዙፍ ክለቦች ኢንተር ሚላን እና ኤሲ ምላን ራዳር ውስጥ ይገኛል። የተጭዋቹ ኮንትራት በመጪው ክረምት ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል።
(Source: Calciomercato)

.

➦  ቶተንሃሞች የባርሴሎናውን አጥቂ ማልኮልም ከባርሴሎና ለማዛወር ከፍተኛውን ፍላጎት ያሳደሩ ብቸኛ ክለብ ናቸው። ቶተንሃሞች ተጭዋቹን የሚለቁላቸው ከሆነ ለዝውውሩ የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ያወጣውን €41M ለመክፈል ፍቃደኞችም ናቸው።  (Dailymail)

.

➦  የጣሊያኑ የቀድሞ ኮከብ ተጭዋች ክርስቲያን ቪየሪ አሁን ላይ ያሉ አጥቂዎች 'ራሳቸውን ማሻሻል የማይፈልጉ ጎል ማግባት ያመማቸው አጥቂዎች ናቸው' ሲል ተችቷል።

"በዚህ ሰአት ጥሩ አጥቂ ለመሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኢንትታግራም ተከታዮች ካሉህ ብቻ በቂ ነው"   (Dailymail)

.

➦  ኔይማር ወደ ባርሴሎና የተዛቀረበት ህገወጥ በሙስና የተጨማለቀ የዝውውር ሂደት ተጭዋቹን ለስድስት አመታት ለእስር የሚዳርግ ተግባር ነው ሲሉ አንድ የስፔን ዳኛ ተናግረዋል።   (ESPN)




No comments:

Post a Comment