ቤትዎ ቁጭ ብለው የሚሰሩት ስራ መጣልዎ! እንዴት ከታች ምስሉን ተጫኑ

Thursday 8 November 2018

ሃሙስ ምሽት የወጡ ከ20 በላይ የዝውውር እና ሌሎችም ዜናዎች

ማንችስተር ዩናይትዶች ለአንቶኒ ማርሻል የጠየቀውን ሳምንታዊ የ£190,000 ደሞዝ የሚያገኝበትን ኮንትራት ቦነሱንም ጨምሮ ሊሰጡት ተዘጋጅተዋል።
(Source: Sun Sport)

.

ሪያል ማድሪዶች ኬይላን ምባፔን በ2017 ላይ በ€214m የዝውውር ሂሳብ ሊያስፈርሙት ከክለቡ ሞናኮ ጋር ከስምምነት ደርሰው ነበር። ሆኖም ተጭዋቹ በፓሪስ በመወለዱ ምክንያት ለፒ.ኤስ.ጂ መፈረምን መርጦ ወደዛው ተዛውሯል።   (Source: L'Equipe)

.

ሊዮን ቤይሊ በክረምቱ ከማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትዶች ቀርቦለት የነበረውን የእናዛውርህ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በባየር ሌቨርኩሰን መቆየቱን ተናገረ።   (Source: MEN)

ሊዮን ቤይሊ ለFourFourTwo: "ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ማን.ሲቲ፣ ቼልሲ፣ ሊቨርፑል ሁሉም ትልልቅ ክለቦች ናቸው። ሁሉም ሊወስዱኝ ፈልገው ነበር። ሆኖም ወሳኙ ነገር አሁን መማር ባለብኝ ቦታ እና ስፍራ መቆየቴ ለኔ ጠቃሚ ውሳኔ ነው። በፍትነት ትልቅ ክለብ መቀየር ለእድገቴም መልካም አይደለም። ምክንያቱም ገና ካሁኑ ትልቅ ክለብ ከገባህ በቀጣይስ ለማደግ ወደየትኛው ክለብ ለመዛወር ትጥራለህ?"

.

ጆዜ ሞሪንዎ ስለ ጁቬንቱስ ደጋፊዎች: “እኔ እነሱን አላንቋሸሽኩም። ያደረኩት ትንሽ ነገር ነው። ተጭዋቾቻቸውን አከብራለሁ ሁሉንም አከብራለሁ። በልጆቼ እጅጉን በጣም ኮርቻለሁ"   [BT]

"እኔኮ ለ90 ደቂቃ ያህል በደጋፊው ስብጠለጠል ነበር። የኔን ቤተሰቦች ሲያንኬስሱ ነበር። እዚህ የመጣሁት ስራዬን ለመስራት ነው እንጂ ለስድድብ አይደለም። በመጨረሻው ደቂቃ ማንንም አልተተናኮልኩም። ድምፃቸውን ከፍ እንዲያደርጉ ጆሮዬን ይዤ ጠይቄያቸዋለሁ። ምናልባት ይህን ማድረግ ላይኖርብኝ ይችላል። ወይም ያደረኩበት መንገድ መጥፎ ሊሆን ይችላል"  [Sky Italia]

.

ጋሬዝ ቤል በክረምቱ ማንቸስተር ዩናይትድን ሊቀላቀሉ ይችላሉ ከተባሉት ተጭዋቾች መሃከል በክለቡ ቀዳሚው የግዢ እቅድ ውስጥ ተይዟል። ዩናይትዶች ተጭዋቹን በቅናሽ ዋጋ እንደሚያዛውሩት ተስፋ አድርገዋል።   (Don Balon)

.

ሽኮድራን ሙስታፊ ስለ ኡናይ ኤምሬ ተፅህኖ: “ለኔ በግሌ እርሱ ማለት ከእያንዳንዱ ተጭዋች ምን እንደሚጠብቅ ጠንቅቆ የሚያውቅ ድንቅ አሰልጣኝ ነው። ማድረግ ያለብህን በግልፅ ይነግርሃል። በተመሳሳይ መልኩም ሜዳ ውስጥ ነፃነቱን ይሰጥሃል"

.

አርሰናሎች የ18 አመቱን የባሂያ አማካይ ራሚሬዝን ለማዛወር ፍላጎት አሳድረዋል። ክለቡ ተጭዋቹን በመከታተል ላይ ይገኛል። በጥር የዝውውር መስኮት ላይ በይፋ ጥያቄያቸውን ለክለቡ ለማቅረብም ዝግጁ ናቸው። [Football_LDN]

ባሂያ በሃገራቸው ብራዚል ሊግ ክለቦች የሚመጣላቸውን የእናዛውረው ጥያቄ በሙሉ ውድቅ ለማድረግ ዝግጁ ሲሆኑ ከወደ አውሮፓ ክለቦች የሚቀርብላቸው ጥያቄ ካለ ግን ሊያጤኑት ዝግጁ ናቸው። አርሰናሎችም የታዳጊው ብራዚላዊ ባለተሰጥዎ ማረፊያ ይሆናሉ በሚል የተሻለ እድል አግኝተዋል።  [Football_LDN]

.

ሊቨርፑሎች ታዳጊውን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ቪክቶር ክርስቶፈር ዲ ባውንበርግ ዝውውር ጋር ስማቸው ተያይዟል። የጭዋቹ የዋናውን የሪያል ማዮርካ ቡድን ሰብሮ ለመግባት እንደቻለ ተነግሮለታል። ሺክቶር በማዮርካ ታዳጊ ማዕከል ለ3ት አመታት ተጫውቷአል። በየአመቱም የቡድኑ ኮከብ ጎል አግቢ መሆን ችሏል።
(liverpoolecho)

.

አንዲ ሮበርትስ እንደሚያምነው ከሆነ ሊቨርፑሎች በፓሪሰን ዥርሜይን ጋር የሚያደርጉትን የቻምፒየንስ ሊጉን ጨዋታ የማሸነፍ እድል አላቸው። ወደ ቀጣዩ ዙርም እንደሚያልፉ ይተማመናል።

"እያንዳንዱን ጨዋታ እንደምናሸንፍ እናምናለን። እንደዛ ስለምናምንም ነው ለዚህ ውጤታማ ቡድን የበቃነው" -  (skysports)

"እንደ ቡድን መጫወት ይኖርብናል። ተቃራ ቡድን ፋታ በመንሳት ማጥቃት ይገባናል። ቀደም ብለን ጎሎችን በማስቆጠር ጨዋታን አስቀድሞ መግደል እና በራስ መተማመን ማሸነፍ ይኖርብናል"

.

ራሂም ስተርሊንግ ስለ ፔናሊቲው ክስተት: "የፈለኩት ኳሷን ቺፕ ማድረግ ነበር። ምን እንደተፈጠረ አላስታውስም። ተጭዋቹ የነካኝም አይመስለኝም። ዳኛውን መልሼ ይቅርታ ጠይቄዋለሁ"

.

አንቶኔ ጋሬዝማን ለKicker ጋዜጣ: "ለኔ ማንቸስተር ሲቲዎች የቻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ የማንሳት የተሻለ እድል አላቸው። ምክንያቱም እነርሱ ፔፕ ጋርዲዮላን ይዘዋል"

.

ሚሼል ባላክ እንደሚያምነው ከሆነ የቀድሞ ክለቡ ቼልሲዎች በዘንድሮው የፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ላይ የማንቸተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ተፎካካሪዎች እንደሆኑ ያምናል።  ቡድኑ በሞሪዚዮ ሳሪ ስል እንደተሻሻለ ያስባል።  (90min)

.

አንቶኒዮ ኮንቴ ቼልሲዎች ስላባረሩአቸው በካሳ መልክ የ£8.7m ክፍያ እንዲከፍላቸው ጠይቀዋል። እንዲሁም ሰውየው ኮንትራታቸውን ሳያጠናቅቁ ለተሰናበቱበት የአመቱን ሙሉ ክፍያ ሂሳብ £11m ጨምረው እንዲከፍሏቸው ጠይቀዋል።   (90min)

.

አልቫሮ ሞራታ በባለፈው የውድድር አመት ላይ ላሳየው መጥፎበቋም ደጋፊዎቹን ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን አሁን ግን በቼልሲና ለንደን ፍፁም ደስተኛ በመሆኔ ወደ ቀድሞ አቋሜ እመለሳለሁ ብሏል።
(90min)

.

የLA Galaxyው አጥቂ ዝላታን ኢቭራሞቪች በጥር የዝውውር መስኮት ላይ ወደ አውሮፓ ክለቦች ይዛወራል የሚለውን ዘገባ አጣጥሎታል።
(Source: SkySports)

.

ጁቬንቱሶች ተከላካያቸውን መሃዲ ቤናሺያን በመሸጥ በሚያገኙት ገንዘብ ላይ ጨምረው በ €60m ከፍተኛ ግምት የተሰጠውን የአያክስ መሃል ተከላካይ ማቲያስ ዲ ሊጅትን ማስፈረም ይፈልጋሉ።
(Source: Tuttosport)

.

ጁቬንቱሶች ፖል ፓግባን ስለሚያዛውሩበት ሁኔታ ከወኪሉ ሚኖ ራዮላ ጋር በተደጋጋሚ ግዜ ንግግር እያደረጉ እንደሚገኝ ተገለፀ። ፈረንሳዊውን ኢንተርናሽናል ወደ ቱሪን የመመለስ ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው።  (Source: Tuttosport)

No comments:

Post a Comment